La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 51:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ከሰ​ይፍ ያመ​ለ​ጣ​ችሁ ሆይ! ሂዱ፤ አት​ቁሙ፤ በሩቅ ያላ​ች​ሁም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አስቡ፤ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በል​ባ​ችሁ አስቡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከሰይፍ ያመለጣችሁ ሆይ፤ ሂዱ! ጊዜ አትፍጁ፤ በሩቅ ምድር ያላችሁ እግዚአብሔርን አስታውሱ፤ ኢየሩሳሌምንም አስቧት።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከሰይፍ ያመለጣችሁ ሆይ! ሂዱ፥ አትቁሙ፤ በሩቅ ስፍራ ሆናችሁ ጌታን አስታውሱ፥ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡአት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር በባቢሎን ላሉት ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “እናንተ ከሞት የተረፋችሁ ሕዝቤ! ሳትዘገዩ ሂዱ! በሩቅ ሀገር ሆናችሁ እኔን እግዚአብሔርን አስታውሱ! ኢየሩሳሌምን በልባችሁ አስቡ!

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከሰይፍ ያመለጣችሁ ሆይ፥ ሂዱ፥ አትቁሙ፥ እግዚአብሔርን ከሩቅ አስቡ፥ ኢየሩሳሌምንም በልባችሁ አስቡ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 51:50
24 Referencias Cruzadas  

ከባ​ቢ​ሎን ውጡ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ኰብ​ልሉ፤ በእ​ል​ልታ ድምፅ ተና​ገሩ፤ ይህም ይሰማ፤ እስከ ምድ​ርም ዳርቻ ድረስ አው​ሩና፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ባር​ያ​ውን ያዕ​ቆ​ብን ታድ​ጎ​ታል” በሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የተ​ቤ​ዣ​ቸው ይመ​ለ​ሳሉ፤ ወደ ጽዮ​ንም በደ​ስ​ታና በሐ​ሤት ይመ​ጣሉ፤ የዘ​ለ​ዓ​ለ​ምም ክብር በራ​ሳ​ቸው ላይ ይሆ​ናል፤ ደስ​ታ​ንና ተድ​ላን ያገ​ኛሉ፤ ኀዘ​ንና ልቅ​ሶም ይወ​ገ​ዳሉ።


ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም ሆይ፥ ትቢ​ያን አራ​ግፊ፤ ተነሺ፥ ተቀ​መጪ፤ ምር​ኮ​ኛ​ዪቱ የጽ​ዮን ልጅ ሆይ፥ የአ​ን​ገ​ት​ሽን እስ​ራት ፍቺ።


“ለራ​ስሽ የመ​ን​ገድ ምል​ክት አድ​ርጊ፥ መን​ገ​ድ​ንም የሚ​መሩ ዐም​ዶ​ችን ትከዪ፤ ልብ​ሽ​ንም ወደ ሄድ​ሽ​በት መን​ገድ ወደ ጥር​ጊ​ያው አቅኚ፤ አንቺ የእ​ስ​ራ​ኤል ድን​ግል ሆይ! ተመ​ለሺ፤ ወደ እነ​ዚ​ህም ወደ ከተ​ሞ​ችሽ እያ​ለ​ቀ​ስሽ ተመ​ለሺ።


ከሰ​ይ​ፍም የሚ​ያ​መ​ልጡ በቍ​ጥር ጥቂ​ቶች ሰዎች ከግ​ብፅ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመ​ለ​ሳሉ፤ ሊቀ​መ​ጡም ወደ ግብፅ ምድር የገ​ቡት የይ​ሁዳ ቅሬታ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእ​ነ​ርሱ የማ​ና​ችን ቃል እን​ዲ​ጸና ያው​ቃሉ።


ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ንም ምድር ውጡ፤ በበ​ጎ​ችም ፊት እንደ እባ​ቦች ሁኑ።


“ሕዝቤ ሆይ! ከመ​ካ​ከ​ልዋ ውጡ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽኑ ቍጣ ራሳ​ች​ሁን አድኑ።


ከባ​ቢ​ሎን መካ​ከል ሽሹ፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ች​ሁም ነፍ​ሳ​ች​ሁን አድኑ፤ በበ​ደ​ልዋ አት​ጥፉ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በቀል ጊዜ ነውና፥ እር​ሱም ብድ​ራ​ቷን ይከ​ፍ​ላ​ታ​ልና።


በዚያ በተ​ማ​ረ​ኩ​በት በአ​ሕ​ዛብ ዘንድ ከእ​ና​ንተ የዳ​ኑት ያስ​ቡ​ኛል፤ ለሰ​ሰ​ኑ​በት፥ ከእ​ኔም ለራ​ቁ​በት ለል​ቡ​ና​ቸው፥ ለሰ​ሰኑ፥ ጣዖ​ት​ንም ለተ​ከ​ተሉ ለዓ​ይ​ኖ​ቻ​ቸው ማልሁ፤ ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ሁሉ እን​ዳ​መ​ለኩ መጠን ስለ ሥራ​ቸው ክፋት ፊታ​ቸ​ውን ይነ​ጫሉ።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤