ኤርምያስ 49:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእግዚአብሔር ዘንድ መስማትን ሰምቻለሁ፤ በአሕዛብ ሀገሮች ተሰብሰቡ፤ በእርስዋም ላይ ኑ፤ እርስዋንም ውጓት፥ የሚል መልእክተኛ ተልኳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእግዚአብሔር ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ፤ “እርሷን ለመውጋት ተሰብሰቡ፤ ለጦርነትም ውጡ” የሚል መልእክተኛ ወደ አሕዛብ ተልኳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከጌታ ዘንድ መልእክት ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ “ተሰብሰቡ፥ በእርሷም ላይ ኑ ለጦርነትም ተነሡ” የሚል መልእክተኛ ተልኮአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ መልእክት ከእግዚአብሔር ሰምቼአለሁ፤ “በኤዶም ሕዝብ ላይ አደጋ ለመጣል ተሰብሰቡ! ለጦርነትም ተነሡ!” ብሎ የሚናገር መልእክተኛ ወደ ሕዝቦች ተልኮአል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእግዚአብሔር ዘንድ ወሬ ሰምቻለሁ በአሕዛብም መካከል፦ ተሰብሰቡ፥ በእርስዋም ላይ ኑ ለሰልፍም ተነሡ የሚል መልእክተኛ ተልኮአል። |
እነሆ፥ መንፈስን በላዩ እሰድዳለሁ፤ ወሬንም ይሰማል፤ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት” አላቸው።
“ፍላጾችን አዘጋጁ፤ ጕራንጕሬዎችንም ሙሉ፤ እግዚአብሔር ያጠፋት ዘንድ ቍጣው በባቢሎን ላይ ነውና የሜዶንን ንጉሥ መንፈስ አስነሥቶአል፤ የእግዚአብሔር በቀል የመቅደሱ በቀል ነውና።
በምድርም ከሚሰማ ወሬ የተነሣ አትፍሩ፤ ልባችሁም የዛለ አይሁን፤ በአንድ ዓመት ወሬ ይመጣል፤ ከዚያም በኋላ በሌላው ዓመት ወሬ ይመጣል፤ በምድርም ላይ ግፍ ይነግሣል፤ አለቃም በአለቃ ላይ ይነሣል።