La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 34:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ነገር ግን የይ​ሁዳ ንጉሥ ሴዴ​ቅ​ያስ ሆይ! የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስማ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስለ አንተ እን​ዲህ ይላል፦ በሰ​ይፍ አት​ሞ​ትም፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘ነገር ግን፣ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፤ በሰይፍ አትሞትም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ነገር ግን፥ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ! የጌታን ቃል ስማ፤ ጌታ ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ ‘በሰይፍ አትሞትም፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሴዴቅያስ ሆይ፥ እኔ ስለ አንተ የምለውን ስማ፤ በጦርነት ላይ አትሞትም፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ነገር ግን፥ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፥ እግዚአብሔር ስለ አንተ እንዲህ ይላል፦ በሰይፍ አትሞትም፥ በሰላም ትሞታለህ እንጂ፥

Ver Capítulo



ኤርምያስ 34:4
7 Referencias Cruzadas  

ሚክ​ያ​ስም አለ፥ “እን​ዲህ አይ​ደ​ለም፤ እን​ግ​ዲህ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዙ​ፋኑ ተቀ​ምጦ፥ የሰ​ማይ ሠራ​ዊት ሁሉ በቀ​ኙና በግ​ራው፤ ቆመው አየሁ።”


የያ​ዕ​ቆብ ቤት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ወገ​ኖች ሁሉ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ሴዴ​ቅ​ያ​ስም ወደ ባቢ​ሎን ይገ​ባል፤ እኔም እስ​ክ​ጐ​በ​ኘው ድረስ በዚያ ይኖ​ራል፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ጋር ብቷጉ ምንም አይ​ቀ​ና​ች​ሁም።”


አን​ተም በር​ግጥ ትያ​ዛ​ለህ፤ በእ​ጁም አል​ፈህ ትሰ​ጣ​ለህ እንጂ ከእጁ አታ​መ​ል​ጥም፤ ዐይ​ን​ህም የባ​ቢ​ሎ​ንን ንጉሥ ዐይን ታያ​ለች፤ እር​ሱም ከአ​ንተ ጋር አፍ ለአፍ ይና​ገ​ራል፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ትገ​ባ​ለህ።


ነገር ግን በሰ​ላም ትሞ​ታ​ለህ፥ ከአ​ንተ በፊት እንደ ነበሩ እንደ ዱሮ ነገ​ሥ​ታት አባ​ቶ​ችህ እሳት ይቃ​ጠ​ል​ላ​ቸው እንደ ነበር እን​ዲሁ ያቃ​ጥ​ሉ​ል​ሃ​ልና፦ ወየው! ጌታ ሆይ! እያሉ ያለ​ቅ​ሱ​ል​ሃል፤ እኔ ቃልን ተና​ግ​ሬ​አ​ለ​ሁና” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


“በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በር ቁም፤ ይህ​ንም ቃል እን​ዲህ ብለህ ተና​ገር፦ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትሰ​ግዱ ዘንድ በእ​ነ​ዚህ በሮች የም​ት​ገቡ ከይ​ሁዳ ያላ​ችሁ ሁሉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።