በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም፥ “ሁሉ በኀጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች ስለ ልጆች አይሙቱ፤ ልጆችም ስለ አባቶች አይሙቱ” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም።
ኤርምያስ 31:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፤ ጮርቃውን የወይን ፍሬ የሚበላም ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን፣ እያንዳንዱ በገዛ ኀጢአቱ ይሞታል፤ ጐምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሰው ሁሉ የራሱን ጥርስ ይጠርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፤ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ የተጠረሱ ይሆናሉ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህ መሆኑ ቀርቶ ጎምዛዛ የወይን ፍሬ የሚበላ ሰው ሁሉ የገዛ ራሱን ጥርስ ብቻ ያጠርሳል፤ እያንዳንዱም በገዛ ራሱ ኃጢአት ይሞታል።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ሰው ሁሉ በገዛ በደሉ ይሞታል፥ መራራውን የወይን ፍሬ የሚበላ ሁሉ ጥርሶቹ ይጠርሳሉ። |
በሙሴ ሕግ መጽሐፍም እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔርም፥ “ሁሉ በኀጢአቱ ይሙት እንጂ አባቶች ስለ ልጆች አይሙቱ፤ ልጆችም ስለ አባቶች አይሙቱ” ብሎ እንዳዘዘ የነፍሰ ገዳዮቹን ልጆች አልገደላቸውም።
ኀጢአትን የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች፤ ልጅ የአባቱን ኀጢአት አይሸከምም፤ አባትም የልጁን ኀጢአት አይሸከምም፤ የጻድቁ ጽድቅ በራሱ ላይ ይሆናል፤ የኀጢአተኛውም ኀጢአት በራሱ ላይ ይሆናል።
እነሆ ነፍሳት ሁሉ የእኔ ናቸው፤ የአባት ነፍስ የእኔ እንደ ሆነች እንዲሁ የልጅ ነፍስ የእኔ ናት፤ ኀጢአት የምትሠራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች።
እኔ ጻድቁን፦ በርግጥ በሕይወት ትኖራለህ ባልሁ ጊዜ፥ እርሱ በጽድቁ ታምኖ ኀጢአት ቢሠራ በሠራው ኀጢአት ይሞታል እንጂ ጽድቁ አይታሰብለትም።
ኀጢአተኛውን፦ ኀጢአተኛ ሆይ! በርግጥ ትሞታለህ ባልሁ ጊዜ፥ ኀጢአተኛውን ከክፉ መንገዱ ታስጠነቅቅ ዘንድ ባትናገር፥ ያ ኀጢአተኛ በኀጢአቱ ይሞታል፤ ደሙን ግን ከእጅህ እፈልጋለሁ።
“አባቶች ስለ ልጆቻቸው አይገደሉ፤ ልጆችም ስለ አባቶቻቸው አይገደሉ፤ ነገር ግን ሁሉ እያንዳንዱ በኀጢአቱ ይገደል።