በገለዓድ ቴስባን የነበረው ቴስብያዊው ነቢዩ ኤልያስ አክዓብን፥ “በፊቱ የቆምሁት የኀያላን አምላክ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ዝናብም ጠልም አይወርድም” አለው።
ያዕቆብ 5:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፤ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ተኩል ዝናብ አልዘነበም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፤ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ተኩል ዝናብ አልዘነበም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልያስ እንደ እኛ ሰው ነበረ፤ ነገር ግን ዝናብ እንዳይዘንብ አጥብቆ በጸለየ ጊዜ ለሦስት ዓመት ተኩል በምድር ላይ ምንም ዝናብ አልዘነበም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልያስ እንደ እኛ የሆነ ሰው ነበረ፥ ዝናብም እንዳይዘንብ አጥብቆ ጸለየ፥ በምድርም ላይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር አልዘነበም፤ ሁለተኛም ጸለየ፥ |
በገለዓድ ቴስባን የነበረው ቴስብያዊው ነቢዩ ኤልያስ አክዓብን፥ “በፊቱ የቆምሁት የኀያላን አምላክ የእስራኤል አምላክ ሕያው እግዚአብሔርን! ከአፌ ቃል በቀር በእነዚህ ዓመታት ዝናብም ጠልም አይወርድም” አለው።
ከብዙ ቀንም በኋላ በሦስተኛው ዓመት፥ “ሂድ ለአክዓብ ተገለጥ፤ በምድር ላይም ዝናም እሰጣለሁ” የሚል የእግዚአብሔር ቃል ወደ ኤልያስ መጣ።
እውነት እላችኋለሁ፤ በነቢዩ በኤልያስ ዘመን በምድር ሁሉ ብርቱ ረኃብ እስኪሆን ድረስ ሰማይ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር በተዘጋበት ጊዜ ብዙ መበለቶች በእስራኤል ውስጥ ነበሩ።
እንዲህም አሉአቸው፥ “እናንተ ሰዎች፥ ይህን ነገር ለምን ታደርጋላችሁ? እኛስ እንደ እናንተ የምንሞት ሰዎች አይደለንምን? ነገር ግን ይህን ከንቱ ነገር ትታችሁ ሰማይና ምድርን፥ ባሕርንም በውስጣቸውም ያለውን ሁሉ ወደ ፈጠረ ወደ ሕያው እግዚአብሔር ትመለሱ ዘንድ ወንጌልን እናስተምራችኋለን።
እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን ሕዝቡን አልጣላቸውም፤ ኤልያስ እስራኤልን ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል በከሰሳቸው ጊዜ መጽሐፍ ያለውን አታውቁምን?
እነዚህ ትንቢት በሚናገሩበት ወራት ዝናብ እንዳይዘንብ ሰማይን ሊዘጉ ሥልጣን አላቸው፤ ውሕሃዎችንም ወደ ደም ሊለውጡ በሚፈልጉበትም ጊዜ ሁሉ በመቅሠፍት ሁሉ ምድርን ሊመቱ ሥልጣን አላቸው።