ኢሳይያስ 48:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፤ ከአፌም ወጥቶአል፤ ድንገትም ያደረግሁት ምስክር ሆኖአል፤ እርሱም ተፈጽሞአል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቀደሙትን ነገሮች ከብዙ ዘመን በፊት ተናግሬአለሁ፤ ከአፌ ወጥተዋል፤ እንዲታወቁም አድርጌአለሁ፤ እኔም ድንገት ሠራሁ፤ እነርሱም ተፈጸሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፥ ከአፌም ወጥቶአል፥ አሳይቼውማለሁ፤ ድንገት አድርጌው ተፈጽሞዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ለእስራኤል እንዲህ ይላል፦ “ወደ ፊት ስለሚሆነው ነገር ከብዙ ጊዜ በፊት ተናገርኩ፤ እርሱንም በፍጥነት እንዲከናወን አደረግሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቀድሞውን ነገር ከጥንት ተናግሬአለሁ፥ ከአፌም ወጥቶአል አሳይቼውማለሁ፥ ድንገት አድርጌዋለሁ ተፈጽሞማል። |
ስለዚህ ይህ በደል አዘብዝቦ ለመፍረስ እንደ ቀረበ፥ አፈራረሱም ፈጥኖ ድንገት እንደሚመጣ እንደ ከተማ ቅጥር ይሆንባችኋል።
የተቈጣኸው ቍጣና ትዕቢትህ ወደ ጆሮዬ ደርሶአልና ሰለዚህ ስናጋዬን በአፍንጫህ፥ ልጓሜንም በከንፈርህ አደርጋለሁ፤ በመጣህበትም መንገድ እመልስሃለሁ።
እነሆ፥ መንፈስን በላዩ እሰድዳለሁ፤ ወሬንም ይሰማል፤ ወደ ምድሩም ይመለሳል፤ በምድሩም በሰይፍ እንዲወድቅ አደርጋለሁ በሉት” አላቸው።
ይምጡ፤ የሚደርስባችሁንም ይንገሩን፤ ልብም እናደርግ ዘንድ፤ ፍጻሜአቸውንም እናውቅ ዘንድ፥ የቀደሙት ነገሮች ምን እንደ ሆኑ ንገሩን፤ የሚመጡትንም አሳዩን።
እነሆ የቀድሞው ነገር ተፈጸመ፤ አዲስ ነገርንም እናገራለሁ፤ አስቀድሞም ሳይነገር እርሱን አስታውቃችኋለሁ።”
አሕዛብ ሁሉ በአንድነት ተሰበሰቡ፤ አለቆችም ተከማቹ፤ ይህን ማን ይናገራል? የቀድሞውንስ ማን ይነግራችኋል? ይጸድቁ ዘንድ ምስክሮቻቸውን ያምጡ፤ ሰምተውም፦ እውነትን ይናገሩ።
የሚናገሩ ከሆነ ከጥንት ጀምሮ ይህን ምስክርነት ያደረገ ማን እንደ ሆነ በአንድነት ያውቁ ዘንድ ይቅረቡ። ያሳየሁም የተናገርሁም እኔ እግዚአብሔር አይደለሁምን? ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ የለም፤ እኔ ጻድቅ አምላክና መድኀኒት ነኝ፥ እንደ እኔም ያለ ማንም የለም።