La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 48:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህ​ንም ስሙ፤ እኔ ከጥ​ንት ጀምሬ በስ​ውር አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ከሆ​ነ​በት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበ​ርሁ፤ አሁ​ንም ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርና መን​ፈሱ ልከ​ው​ኛል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ወደ እኔ ቅረቡ፤ ይህን ስሙ፤ “ከመጀመሪያ ጀምሮ በስውር አልተናገርሁም፤ ሲፈጸምም እኔ እዚያው ነበርሁ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፤ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርኩም፤ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርኩ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ወደ እኔ ቀርባችሁ ይህን ስሙ፤ ከመጀመሪያ ጀምሮ የተናገርኩት በምሥጢር አይደለም፤ ከሆነበት ጊዜ ጀምሮ እኔ እዚያ ነበርኩ።” አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ወደ እኔ ቅረቡ ይህንም ስሙ፥ እኔ ከጥንት ጀምሬ በስውር አልተናገርሁም፥ ከሆነበት ዘመን ጀምሮ እኔ በዚያ ነበርሁ፥ አሁንም ጌታ እግዚአብሔርና መንፈሱ ልከውኛል።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 48:16
13 Referencias Cruzadas  

እና​ንተ አሕ​ዛብ ሆይ፥ ቅረቡ፤ እና​ን​ተም አለ​ቆች ሆይ፥ አድ​ምጡ፤ ምድ​ርና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ፥ ዓለ​ምና በው​ስ​ጥ​ዋም ያሉ ሕዝብ ሁሉ ይስሙ።


ደሴ​ቶች ሆይ፥ ወደ እኔ ተመ​ለሱ፤ አለ​ቆች ኀይ​ላ​ቸ​ውን ያድ​ሳ​ሉና በአ​ን​ድ​ነት ቀር​በው ፍር​ድን ይና​ገሩ።


ከጥ​ንት ጀምሮ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ ከእ​ጄም የሚ​ያ​መ​ልጥ የለም፤ እሠ​ራ​ለሁ፤ ወደ ኋላስ የሚ​መ​ልስ ማን ነው?


በስ​ውር ወይም በጨ​ለማ ስፍራ አል​ተ​ና​ገ​ር​ሁም፤ ለያ​ዕ​ቆብ ዘር፦ በከ​ንቱ ፈል​ጉኝ አላ​ል​ሁም፤ ጽድ​ቅን የም​ና​ገር፥ ቅን ነገ​ር​ንም የም​ና​ገር እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።


እና​ንተ የኃ​ጥ​ኣን ልጆች፥ የዘ​ማ​ው​ያ​ንና የጋ​ለ​ሞ​ታ​ዪቱ ዘር፥ ወደ​ዚህ ቅረቡ።


“የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈስ በላዬ ነው፤ ስለ​ዚህ ቀብቶ ለድ​ሆች የም​ሥ​ራ​ችን እነ​ግ​ራ​ቸው ዘንድ፥ ለተ​ማ​ረ​ኩ​ትም ነጻ​ነ​ትን እሰ​ብ​ክ​ላ​ቸው ዘንድ፥ ያዘ​ኑ​ት​ንም ደስ አሰ​ኛ​ቸው ዘንድ፥ ዕው​ሮ​ችም ያዩ ዘንድ፥ የተ​ገ​ፉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥ የታ​ሰ​ሩ​ት​ንም እፈ​ታ​ቸው ዘንድ፥ የቈ​ሰ​ሉ​ት​ንም አድ​ና​ቸው ዘንድ፥


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መልሶ እን​ዲህ አለው፥ “እኔ ለዓ​ለም በግ​ልጥ ተና​ገ​ርሁ፤ አይ​ሁድ ሁሉ በሚ​ሰ​በ​ሰ​ቡ​በት በም​ኵ​ራ​ብም፥ በቤተ መቅ​ደ​ስም ሁል​ጊዜ አስ​ተ​ማ​ርሁ፤ በስ​ው​ርም የተ​ና​ገ​ር​ሁት አን​ዳች ነገር የለም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የላ​ከው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ይና​ገ​ራል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ፈ​ሱን ሰፍሮ አይ​ሰ​ጥ​ምና።