ከጥፍጥፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም ጋሻ የገባው ወርቅ ሦስት ምናን ነው፤ ንጉሡም የሊባኖስ ዱር በተባለው ቤት ውስጥ አኖራቸው።
ኢሳይያስ 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳንም በሮች ይከፍታሉ፤ በዚያም ቀን የከተማይቱን መኳንንት ቤቶች ይበረብራሉ። የዳዊት ቤት መዛግብትንም ይከፍታሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል። በዚያ ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣ የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳንም መጋረጃ ገልጧል። በዚያም ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን የጦር ዕቃ ተመለከትህ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ ምሽጎች ሁሉ ተደምስሰዋል፤ በዚያን ጊዜ በጦር ግምጃ ቤት ውስጥ የተከማቸውን የጦር መሣሪያ ወሰዳችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳንም መጋረጃ ገለጠ፥ በዚያም ቀን በዱር ቤት የነበረውን የጦር ዕቃ ተመለከትህ፥ |
ከጥፍጥፍም ወርቅ ሦስት መቶ ጋሻ አሠራ፤ በአንዱም ጋሻ የገባው ወርቅ ሦስት ምናን ነው፤ ንጉሡም የሊባኖስ ዱር በተባለው ቤት ውስጥ አኖራቸው።
የሊባኖስ ዱር ቤት የሚባል ቤትንም ሠራ፤ ርዝመቱንም መቶ ክንድ፥ ስፋቱንም አምሳ ክንድ፥ ቁመቱንም ሠላሳ ክንድ አደረገ፤ የዋንዛም እንጨት በሦስት ወገን በተሠሩ አዕማድ ላይ ቆሞ ነበር፤ በአዕማዱም ላይ የዋንዛ እንጨት አግዳሚ ሰረገሎች ነበሩ።
አንገትሽ ለሰልፍ ዕቃ መስቀያ እንደ ተሠራ እንደ ዳዊት ግንብ ነው፤ በውስጡም ሺህ የጦር ዕቃና የኀያላን መሣሪያ ሁሉ ተሰቅሎበታል።