እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፥ “ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! ጣዖቶችዋም ሁሉ፥ የእጆችዋም ሥራዎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” አለ።
ኢሳይያስ 21:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለት ፈረሰኞችን ሲጋልቡ አየሁ፤ አንዱ በአህያ ላይ፥ ሁለተኛውም በግመል ላይ ተቀምጦ ነበር፤ ድምፃቸው ግን እንደ ብዙዎች ፈረሰኞች ድምፅ ነበረ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በፈረሶች የሚሳብ፣ ሠረገሎችን ሲያይ፣ በአህያ ላይ የሚቀመጡትን፣ በግመል የሚጋልቡትን ሲመለከት፣ ያስተውል፤ በጥንቃቄም ያስተውል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከብት የሚቀመጡትን፥ ሁለት ሁለት እየሆኑ የሚሄዱት ፈረሰኞች፥ በአህዮች የሚቀመጡትንና በግመሎች የሚቀመጡትን ባየ ጊዜ በጽኑ ትጋት አስተውሎ ተግቶም ያድምጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈረሰኞች ጥንድ ጥንድ ሆነው ሲጋልቡ፥ የአህያና የግመል ጋላቢዎችንም ቢያይ በጥንቃቄ ይመልከታቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከብት የሚቀመጡትን፥ ሁለት ሁለት እየሆኑ የሚሄዱት ፈረሰኞች፥ በአህዮች የሚቀመጡትንና በግመሎች የሚቀመጡትን ባየ ጊዜ በጽኑ ትጋት አስተውሎ ተግቶም ያድምጥ። |
እነሆም፥ በፈረሶች የሚቀመጡ፥ ሁለት ሁለት ሆነው የሚሄዱ ፈረሰኞች ይመጣሉ” ብሎ ጮኸ፤ እርሱም መልሶ፥ “ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! ጣዖቶችዋም ሁሉ፥ የእጆችዋም ሥራዎች ሁሉ በምድር ላይ ተጥለው ደቀቁ” አለ።
አንተም በመልእክተኞችህ በኩል እንዲህ ብለህ እግዚአብሔርን ተገዳደርኸው፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ራስ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥሞቹንም ዝግባዎች፥ የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገባለሁ፤
እኔን ፈጽሞ ብትሰሙ፥ ይላል እግዚአብሔር፤ በሰንበትም ቀን በዚህች ከተማ በሮች ሸክም ባታገቡ፥ የሰንበትንም ቀን ብትቀድሱ፥ ሥራንም ሁሉ ባትሠሩባት፥