La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሆሴዕ 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሰማ​ይን ያጸ​ናሁ፥ ምድ​ር​ንም የፈ​ጠ​ርሁ፥ እጆ​ችም የሰ​ማይ ሠራ​ዊ​ትን ያቆሙ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እኔ ነኝ። እን​ዳ​ት​ከ​ተ​ላ​ቸ​ውም እነ​ር​ሱን አላ​ሳ​የ​ሁ​ህም። ከግ​ብፅ ምድ​ርም ያወ​ጣ​ሁህ እኔ ነኝ። ከእኔ በቀር ሌላ አም​ላክ አት​ወቅ፤ ከእኔ በቀር የሚ​ያ​ድ​ንህ የለ​ምና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“እኔ ግን ከግብጽ ምድር ያወጣሁህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፤ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እኔ ግን ጌታ፥ ከግብጽ ምድር ጀምሬ አምላክህ ነኝ፤ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ አዳኝ የለም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከግብጽ ምድር ያወጣኋችሁ አምላካችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የላችሁም፤ አዳኛችሁም እኔ ብቻ ነኝ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እኔ ግን ከግብጽ ምድር ጀምሬ አምላክህ እግዚአብሔር ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ አምላክ አታውቅም፥ ከእኔም በቀር ሌላ መድኃኒት የለም።

Ver Capítulo



ሆሴዕ 13:4
14 Referencias Cruzadas  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን ከእጄ ያድ​ናት ዘንድ ከሀ​ገ​ሮቹ አማ​ል​ክት ሁሉ ሀገ​ሩን ከእጄ ያዳነ ማን ነው?”


እኔ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መድ​ኀ​ኒ​ትህ ነኝ፤ ግብ​ፅ​ንና ኢት​ዮ​ጵ​ያን ለአ​ንተ ቤዛ አድ​ርጌ፥ ሴዎ​ን​ንም ለአ​ንተ ፋንታ ሰጥ​ቻ​ለሁ።


እስ​ራ​ኤል ሕፃን በነ​በረ ጊዜ ወደ​ድ​ሁት፤ ልጄ​ንም ከግ​ብፅ ጠራ​ሁት፤


እኔም ከግ​ብፅ ምድር ያወ​ጣ​ሁህ አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ፤ እንደ ዓመት በዓል ቀንም እንደ ገና በድ​ን​ኳን አስ​ቀ​ም​ጥ​ሃ​ለሁ።


ኤፍ​ሬ​ምም፥ “ባለ​ጸጋ ሆኜ​አ​ለሁ፤ ሀብ​ት​ንም አግ​ኝ​ቻ​ለሁ፤ በድ​ካ​ሜም ሁሉ ኀጢ​አት የሚ​ሆን በደል አይ​ገ​ኝ​ብ​ኝም” አለ።


ከዚ​ያም የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘ​ብ​ዋን እሰ​ጣ​ታ​ለሁ፤ ምክ​ር​ዋ​ንም በአ​ኮር ሸለቆ እገ​ል​ጣ​ለሁ፤ እንደ ሕፃ​ን​ነ​ትዋ ወራት፥ ከግ​ብ​ፅም እንደ ወጣ​ች​በት ቀን ትዘ​ም​ራ​ለች።


ለእ​ኔም እን​ድ​ት​ሆኚ በመ​ታ​መን አጭ​ሻ​ለሁ፤ አን​ቺም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታው​ቂ​አ​ለሽ።


እኔ ግን ከም​ስ​ጋ​ናና ከኑ​ዛዜ ቃል ጋር እሠ​ዋ​ል​ሃ​ለሁ፤ የድ​ኅ​ነቴ አም​ላክ ሆይ! የተ​ሳ​ል​ሁ​ትን ለአ​ንተ እከ​ፍ​ላ​ለሁ።”


መዳ​ንም በሌላ በማ​ንም የለም፤ ከሰ​ማይ በታች እን​ድ​ን​በት ዘንድ የሚ​ገ​ባን ለሰው የተ​ሰጠ ሌላ ስም ከቶ የለ​ምና።”