እርሱም በዘገየ ጊዜ እነዚያ መላእክት የእርሱን እጅ፥ የሚስቱንም እጅ፥ የሁለቱን ሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ራርቶላቸዋልና።
ዘፍጥረት 43:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፣ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ፥ እስካሁን ሁለት ጊዜ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህን ያህል ባንዘገይ ኖሮ እስከ አሁን ሁለት ጊዜ እዚያ ደርሰን መመለስ በቻልን ነበር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባንዘገይስ ኖሮ አሁን ሁለተኛ ጊዜ በተመለስን ነበር። |
እርሱም በዘገየ ጊዜ እነዚያ መላእክት የእርሱን እጅ፥ የሚስቱንም እጅ፥ የሁለቱን ሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡአቸው፤ እግዚአብሔር ራርቶላቸዋልና።
አባታቸው እስራኤልም እንዲህ አላቸው፥ “ነገሩ እንዲህ ከሆነስ ይህን አድርጉ ፤ ከምድሩ ፍሬ በዓይበታችሁ ይዛችሁ ሂዱ፤ ለዚያም ሰው እጅ መንሻ፥ ጥቂት በለሳን፥ ጥቂት ማር፥ ሽቱ፥ ዕጣን፥ ተምር፥ ለውዝ ውሰዱ።
እኔ እዋሳለሁ፤ ከእጄ ትሻዋለህ፤ ወደ አንተ ባላመጣው፥ በፊትህም ባላቆመው፥ በዘመናት ሁሉ አንተን የበደልሁህ ልሁን።