ዘፍጥረት 36:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዔሳው ልጅ የኤልፋዝ ልጆችም እነዚህ ናቸው፤ ቴማን፥ ኤሞር፥ ሳፍር፥ ጎቶን፥ ቄኔዝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፣ ኦማር፣ ስፎ፣ ጎቶም ቄኔዝ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኤልፋዝም ልጆች እነዚህ ናቸው፥ ቴማን፥ ኦማር፥ ስፎ፥ ጋታም፥ ቄናዝ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኤልፋዝ ልጆች፦ ቴማን፥ ኦማር፥ ጸፎ፥ ጋዕታምና ቀናዝ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኤልፋዝም ልጆች እንዚህ ናቸው፤ ቴማን አማር፥ ስፎ፥ ጎቶም፥ ቄኔዝ። |
ቴምናሕም ለዔሳው ልጅ ለኤልፋዝ ዕቅብት ነበረች፤ አማሌቅንም ለኤልፋዝ ወለደችለት፤ የዔሳውም ሚስት የሐዳሶ ልጆች እነዚህ ናቸው።
ሦስቱም የኢዮብ ወዳጆች ይህን የደረሰበትን ክፉ ነገር ሁሉ ሰምተው ከየሀገራቸው ወደ እርሱ መጡ፤ እነርሱም ቴማናዊው ንጉሥ ኤልፋዝ፥ አውኬናዊው መስፍን በልዳዶስ፥ አሜናዊው ንጉሥ ሶፋር ነበሩ። እነርሱም ሊጐበኙትና ሊያጽናኑት በአንድነት ወደ እርሱ መጡ።
ስለ ኤዶምያስ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በውኑ በቴማን ጥበብ የለምን? ከብልሃተኞችስ ምክር ጠፍቶአልን? ጥበባቸውስ አልቆአልን?