ዘፍጥረት 34:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፥ “ይህችን ብላቴና አጋባኝ” ብሎ ነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፣ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፥ “ይህችን ልጅ አጋባኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አባቱንም “ከዚህች ልጅ ጋር አጋባኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሴኬምም አባቱን ኤሞርን፦ ይህችን ብላቴና አጋባኝ ብሎ ነገረው። |
ልቡናውም በያዕቆብ ልጅ በዲና ፍቅር ተነደፈ፤ ብላቴናዪቱንም ወደዳት፤ ልብዋንም ደስ በሚያሰኛት ነገር ተናገራት።
ያዕቆብም ልጁን ዲናን የኤሞር ልጅ እንዳስነወራት ሰማ፤ ልጆቹም ከከብቶቻቸው ጋር በምድረ በዳ ነበሩ፤ ያዕቆብም ልጆቹ እስኪመጡ ድረስ ዝም አለ።
እኔም ነውሬን ወዴት እጥላታለሁ? አንተም በእስራኤል ዘንድ ከሰነፎች እንደ አንዱ ትሆናለህ፤ እንግዲያስ ለንጉሡ ንገረው፥ እኔንም አይነሣህም” አለችው።
ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁንም አጋቡ፤ እነርሱም ወንዶችና ሴቶች ልጆችን ይውለዱ፤ ከዚያም ተባዙ፤ ጥቂቶችም አትሁኑ።
ወጥቶም ለአባቱና ለእናቱ፥ “በቴምናታ ከፍልስጥኤማውያን ልጆች አንዲት ሴት አይቻለሁ፤ አሁንም እርስዋን አጋቡኝ” አላቸው።