ዘፍጥረት 27:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይስሐቅም ያዕቆብን፥ “ልጄ ሆይ፥ አንተ ልጄ ዔሳው እንደ ሆንህ ወይም እንዳልሆንህ ቅረበኝና ልዳስስህ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሥሐቅም ያዕቆብን፣ “ልጄ ሆይ፤ አንተ በርግጥ ልጄ ዔሳው መሆንህን እንዳውቅ፣ እስኪ ቀረብ በልና ልዳብስህ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይስሐቅም ያዕቆብን፦ “ልጄ ሆይ፥ አንተ ልጄ ዔሳው እንደሆንህ ወይም እንዳልሆንህ እዳስስህ ዘንድ ቅረበኝ” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይስሐቅም “እስቲ ወደ እኔ ቀረብ በልና ልዳብስህ፤ በእርግጥ አንተ ዔሳው ነህን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይስሐቅም ያዕቆብን፦ ልጄ ሆይ አንተ ልጄ ዔሳ እንደ ሆንህ ወይም እንዳልሆንህ እዳስስህ ዘንድ ቅረበኝ አለው። |
ያዕቆብም ወደ አባቱ ወደ ይስሐቅ ቀረበ፤ ዳሰሰውም፤ እንዲህም አለው፥ “ይህ ድምፅ የያዕቆብ ድምፅ ነው፥ እጆች ግን የዔሳው እጆች ናቸው” አለው።