ዘፍጥረት 24:58 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ርብቃንም ጠርተው፥ “ከዚህ ሰው ጋር ትሄጃለሽን?” አሉአት። እርስዋም፥ “አዎን እሄዳለሁ” አለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ርብቃን ጠርተው፣ “ከዚህ ሰው ጋራ መሄድ ትፈቅጃለሽ?” ሲሉ ጠየቋት። እርሷም፣ “አዎን፤ እሄዳለሁ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ርብቃንም ጠርተው፦ “ከዚህ ሰው ጋር ትሄጃለሽን?” አሉአት። እርሷም፦ “እሄዳለሁ” አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ርብቃን ጠሩና “ከዚህ ሰው ጋር መሄድ ትፈልጊያለሽን?” ብለው ጠየቅዋት። እርስዋም “አዎ እሄዳለሁ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ርብቃንም ጠርተው፦ ከዚህ ሰው ጋር ትሄጃለሽን? አሉአት። እርስዋ፦ እሄዳለሁ አለች። |
ማርያምም መልአኩን፥ “እነሆኝ፥ የእግዚአብሔር ባሪያው አለሁ፤ እንደ ቃልህ ይሁንልኝ” አለችው፤ ከዚህ በኋላም መልአኩ ከእርስዋ ዘንድ ሄደ።