ዘፍጥረት 21:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤሜሌክም አብርሃምን፥ “ለብቻቸው ያቆምሃቸው እነዚያ ሰባ ቄቦች በጎች ምንድን ናቸው?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አቢሜሌክም፣ “እነዚህን ሰባት እንስት በጎች ለይተህ ለብቻ ያቆምሃቸው ለምንድን ነው?” ሲል አብርሃምን ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቢሜሌክም አብርሃምን ለብቻቸው ያቆምሃቸው እነዚህ ሰባት ቄቦች በጎች ምንድን ናቸው? አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አቤሜሌክም “እነዚህን ሰባት ሴት በጎች ለይተህ ያቆምካቸው ለምንድን ነው?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቢሜሌክም አብረሃምን፦ ለብቻቸው ያቆምሃቸው እነዚህ ስባት ቄቦች በጎች ምንድር ናቸው? አለው። |
እርሱም፥ “እኔ ይህችን የውኃ ጕድጓድ እንደቈፈርሁ ምስክር ይሆኑልኝ ዘንድ እነዚህን ሰባ ቄቦች በጎች ከእጄ ትወስዳለህ” አለው።
ዔሳውም፥ “ያገኘሁት ይህ ሠራዊት ሁሉ ምንህ ነው?” አለ። እርሱም፥ “በጌታዬ ፊት ሞገስን አገኝ ዘንድ ያደረግሁልህ ነው” አለ።