La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 14:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ር​ሱም የአ​ብ​ራ​ምን የወ​ን​ድም ልጅ ሎጥ​ንና ገን​ዘ​ቡን ይዘው ሄዱ። እርሱ በሰ​ዶም ይኖር ነበ​ርና።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የአብራም ወንድም ልጅ ሎጥ፣ ሰዶም ይኖር ስለ ነበር እርሱንም ማርከው ንብረቱንም ዘርፈው ሄዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአብራም የወንድም ልጅ ሎጥ በሰዶም ይኖር ስለ ነበር እርሱን ማርከው፥ ሀብቱንም ሁሉ ይዘው ሄዱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በሰዶም ይኖር የነበረውን የአብራምን የወንድም ልጅ ሎጥን ደግሞ ከብቱንም ወስደው ሄዱ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 14:12
13 Referencias Cruzadas  

አራ​ንም ሎጥን ወለደ።


ታራም ልጁን አብ​ራ​ም​ንና የልጅ ልጁን የአ​ራ​ንን ልጅ ሎጥን፥ የል​ጁ​ንም የአ​ብ​ራ​ምን ሚስት ምራ​ቱን ሦራን ወሰደ፤ ከእ​ር​ሱም ጋር ወደ ከነ​ዓን ምድር ይሄዱ ዘንድ ከከ​ለ​ዳ​ው​ያን ምድር አወ​ጣ​ቸው። ወደ ካራ​ንም መጡ፤ በዚ​ያም ተቀ​መጡ።


አብ​ራ​ምም ሚስ​ቱን ሦራ​ንና የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥን፥ ያገ​ኙ​ትን ከብት ሁሉና በካ​ራን ያገ​ኙ​አ​ቸ​ውን ሰዎች ይዞ ወደ ከነ​ዓን ምድር ለመ​ሄድ ወጣ፤ ወደ ከነ​ዓ​ንም ምድር ገቡ።


የሰ​ዶ​ም​ንና የገ​ሞ​ራን ፈረ​ሶች ሁሉ፥ ስን​ቃ​ቸ​ው​ንም ሁሉ ይዘው ሄዱ።


አብ​ራ​ምም የወ​ን​ድሙ ልጅ ሎጥ እንደ ተማ​ረከ በሰማ ጊዜ ወገ​ኖ​ቹ​ንና ቤተ​ሰ​ቦ​ቹን ሁሉ ቈጠ​ራ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም ሦስት መቶ ዐሥራ ስም​ንት ሆኑ፤ እስከ ዳን ድረስ ተከ​ትሎ አሳ​ደ​ዳ​ቸው።


የሰ​ዶ​ምን ፈረ​ሶች ሁሉ አስ​መ​ለሰ፤ ደግ​ሞም የወ​ን​ድ​ሙን ልጅ ሎጥ​ንና ንብ​ረ​ቱን፥ ሴቶ​ች​ንና ሕዝ​ቡ​ንም አስ​መ​ለሰ።


የኃ​ጥ​ኣን ሞታ​ቸው ክፉ ነውና፥ በጻ​ድ​ቃን ይስ​ቃሉ።


ማኅ​በ​ሩ​ንም፥ “ከእ​ነ​ዚህ ክፉ​ዎች ሰዎች ድን​ኳን ፈቀቅ በሉ፤ በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እን​ዳ​ት​ጠፉ ለእ​ነ​ርሱ የሆ​ነ​ውን ሁሉ አት​ንኩ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው።


ከሰማይም ሌላ ድምፅ እንዲህ ሲል ሰማሁ “ሕዝቤ ሆይ! በኀጢአትዋ እንዳትተባበሩ ከመቅሠፍትዋም እንዳትቀበሉ ከእርስዋ ዘንድ ውጡ፤


እኔ የምወዳቸውን ሁሉ እገሥጻቸዋለሁ፤ እቀጣቸውማለሁ፤ እንግዲህ ቅና፤ ንስሓም ግባ።