ከእነዚህም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ የሚያሠሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድስቱ ሺህም ጻፎችና ፈራጆች ነበሩ።
ዕዝራ 3:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም፥ ልጆቹም ተሾሙ፤ ወንድሞቹም፥ የይሁዳም ልጆች ቀደምያልና ልጆቹ፥ የኢንሐዳድም ልጆች፥ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ያሠሩ ዘንድ በአንድነት ቆሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ፣ ወንዶች ልጆቹና ወንድሞቹ፣ የዮሖዳያ ዘሮች ቀድምኤልና ወንዶች ልጆቹ፣ የኤንሐዳድ ወንዶች ልጆች፣ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው፣ ሌዋውያኑም ሁሉ የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ሰዎች ለመቈጣጠር በአንድ ላይ ሆኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱ፥ ልጆቹ፥ ወንድሞቹ፥ የይሁዳም ልጆች ቃድሚኤልና ልጆቹ፥ የሔናዳድም ልጆች፥ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን እንዲቆጣጠሩ እንደ አንድ ቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሌዋዊው ኢያሱና ወንዶች ልጆቹ፥ እንዲሁም ዘመዶቹ፥ ቃድሚኤልና ከሖዳዊያ ቤተሰብ ወገን የሆኑ ወንዶች ልጆቹም ሁሉ በአንድነት ተባብረው ቤተ መቅደሱን እንደገና የመሥራቱን ኀላፊነት ተረከቡ፤ የሔናዳድ ዘሮች የሆኑት ሌዋውያንም ይረዱአቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱ፥ ልጆቹና ወንድሞቹ፥ የይሁዳም ልጆች ቀድምኤልና ልጆቹ፥ የኤንሐዳድም ልጆች፥ ልጆቻቸውና ወንድሞቻቸው፥ ሌዋውያንም የእግዚአብሔርን ቤት የሚሠሩትን ያሠሩ ዘንድ በአንድነት ቆሙ። |
ከእነዚህም ውስጥ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ የሚያሠሩት ሃያ አራት ሺህ ነበሩ፤ ስድስቱ ሺህም ጻፎችና ፈራጆች ነበሩ።
ሰዎቹም ሥራውን በመታመን አደረጉ፤ በእነርሱም ላይ የተሾሙት፥ ሥራውንም የሚያሠሩት ሌዋውያን ከሜራሪ ልጆች ይኤትና አብድያስ፥ ከቀዓትም ልጆች ዘካርያስና ሜሱላም ነበሩ። ከሌዋውያንም ወገን በዜማ ዕቃ ዐዋቂዎች፥ የነበሩ ሁሉ፥
በኢየሩሳሌምም ወዳለው ወደ እግዚአብሔር ቤት በመጡ በሁለተኛው ዓመት በሁለተኛውም ወር የሰላትያል ልጅ ዘሩባቤል፥ የኢዮሴዴቅም ልጅ ኢያሱ፥ የቀሩትም ወንድሞቻቸው ካህናትና ሌዋውያን፥ ከምርኮ ወደ ኢየሩሳሌምም የተመለሱት ሁሉ ጀመሩ፤ ሌዋውያንንም ከሃያ ዓመት ጀምሮ ከዚያም በላይ የእግዚአብሔርን ቤት ሥራ እንዲያሠሩት ሾሙአቸው።
ከእርሱም በኋላ የኢንሓዳድ ልጅ ባኒ ከዓዛርያስ ቤት ጀምሮ እስከ ማዕዘኑ እስከ ግንቡመዞሪያ ድረስ ያለውን ሌላውን ክፍል ሠራ።