ለእስራኤልም ልጆች ይነግራቸው ዘንድ አገልጋዩ ሙሴን እንደ አዘዘው በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ።
ዕዝራ 3:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሀገሩም ካሉት አሕዛብ ፈርተው ነበርና መሠዊያውን በስፍራው ላይ አስቀመጡት፤ በጥዋትና በማታም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዙሪያቸው ካሉት አሕዛብ የተነሣ ፍርሀት ቢያድርባቸውም፣ መሠዊያውን በቀድሞው መሠረት ላይ ሠሩ፤ በመሠዊያውም ላይ ጧትና ማታ የሚቀርበውን የሚቃጠል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድሩ ካሉት ሕዝቦች የተነሣ ፈርተው ነበርና፥ መሠዊያውን በስፍራው ላይ አስቀመጡት በጠዋትና በማታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለጌታ አቀረቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የተመለሱት ምርኮኞች በምድሪቱ ከሚኖሩት አሕዛብ ተቃውሞ የተነሣ ፍርሀት ቢያድርባቸውም እንኳ መሠዊያውን በዚያው ቀድሞ በቆመበት ቦታ መልሰው ሠሩት፤ ከዚያም በኋላ የሚቃጠል መሥዋዕት ዘወትር ጠዋትና ማታ በዚያ ላይ እንደገና ማቅረብ ጀመሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአገሩም ካሉት አሕዛብ ፈርተው ነበርና መሠዊያውን በስፍራው ላይ አስቀመጡት፥ በጥዋትና በማታም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር አቀረቡበት። |
ለእስራኤልም ልጆች ይነግራቸው ዘንድ አገልጋዩ ሙሴን እንደ አዘዘው በእግዚአብሔር ሕግ እንደ ተጻፈ ሁሉ ለሚቃጠለው መሥዋዕት በሚሆነው መሠዊያ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁልጊዜ ጥዋትና ማታ ለእግዚአብሔር ያቀርቡ ዘንድ።
‘ይህን ዕቃ ይዘህ ሂድ፤ በኢየሩሳሌምም ባለው መቅደስ በቦታው አኑረው፤ የእግዚአብሔርም ቤት በስፍራው ይሠራ’ አለው።