በነጋም ጊዜ መንፈሱ ታወከችበት፤ የግብፅ ሕልም ተርጓሚዎችንና ጠቢባንን ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን ሕልሙን የሚተረጕምለት አልተገኘም።
ዘፀአት 7:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ፈርዖን ጠቢባኑንና መተተኞቹን ጠራ፤ የግብጽ አስማተኞችም በድብቅ ጥበባቸው ያንኑ አደረጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ጠቢባንንና አስማተኞችን ጠራ፤ የግብጽም አስማተኞች ደግሞ በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህም በኋላ ፈርዖን ጠቢባኑንና አስማተኞቹን ጠራ፤ እነርሱም በአስማታቸው እንደዚሁ አደረጉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም ጠቢባንንና መተተኞችን ጠራ፤ የግብፅም ጠንቍዮች በአስማታቸው እንዲሁ ደግሞ አደረጉ። |
በነጋም ጊዜ መንፈሱ ታወከችበት፤ የግብፅ ሕልም ተርጓሚዎችንና ጠቢባንን ሁሉ ልኮ አስጠራቸው፤ ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን ሕልሙን የሚተረጕምለት አልተገኘም።
የግብፅም ጠንቋዮች በአስማታቸው እንዲሁ አደረጉ፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረ የፈርዖን ልብ ጸና፤ አልሰማቸውምም።
የግብፅ ጠንቋዮችም በአስማታቸው ቅማል ያወጡ ዘንድ እንዲሁ አደረጉ፤ ነገር ግን አልቻሉም፤ ቅማሉም በሰውና በእንስሳ ላይ ነበረ።
ወንዙም ጓጕንቸሮችን ያፈላል፤ ወጥተውም ወደ ቤትህ፥ ወደ መኝታ ቤትህ፥ ወደ አልጋህም፥ ወደ ሹሞችህም ቤት፥ በሕዝብህም ላይ፥ ወደ ቡሃቃዎችህም፥ ወደ ምድጃዎችህም ይገባሉ፤
እናንተ ሰነፎች የገላትያ ሰዎች ሆይ፥ ለዐይን በሚታየው እውነት እንዳታምኑ ማን አታለላችሁ? እርሱም እንዲሰቀል አስቀድሞ የተጻፈለት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
እንግዲህ በሽንገላቸው ያስቱ ዘንድ በሚተናኰሉ ሰዎች ተንኰል ምክንያት በትምህርት ነፋስ ሁሉ ወዲያና ወዲህ እየተፍገመገምንና እየተንሳፈፍን ሕፃናት አንሁን።
ይድኑ ዘንድ የእውነት ፍቅር ስላልተቀበሉ ለሚጠፉ፥ የእርሱ መምጣት በተአምራት ሁሉና በምልክቶች በሐሰተኞች ድንቆችም በዐመፅም መታለል ሁሉ እንደ ሰይጣን አሠራር ነው።
ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው እውነትን ይቃወማሉ።
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛው ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።
ፍልስጥኤማውያንም ካህናትንና ምዋርተኞችን ጠንቋዮችንም ጠርተው፥ “በእግዚአብሔር ታቦት ላይ ምን እናድርግ? ወደ ስፍራዋስ በምን እንስደዳት? አስታውቁን” አሉ።