ዘፀአት 14:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት መቶ የተመረጡ ሰረገሎችንም፥ የግብፅንም ፈረሶች ሁሉ ወስዶ ሁሉንም ከሦስት ከፈላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስት መቶ ምርጥ ሠረገላዎችን ከሌሎች የግብጽ ሠረገላዎች ጋራ ከነጦር አዛዦቻቸው አሰልፎ ተነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስት መቶ የተመረጡ ሰረገሎችን፥ የግብጽንም ሰረገሎችን ሁሉ፥ የጦር አዛዦች በእያንዳንዱ ሠረገላ ላይ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስድስት መቶ ምርጥ ሠረገሎችን ጨምሮ በግብጽ ያሉትን ሠረገሎች ሁሉ አሰለፈ፤ የጦር አዛዦችንም መደበላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስት መቶ የተመረጡ ሰረገሎችንም፥ የግብፅንም ፈረሶች ሁሉ፥ በእያንዳንዱም ሰረገላ ሁሉ ላይ ሦስተኞችን ወሰደ። |
እግዚአብሔርም የግብፅን ንጉሥ የፈርዖንንና የሹሞቹን ልብ አጸና፤ እርሱም የእስራኤልን ልጆች አሳደደ፤ የእስራኤልም ልጆች ከፍ ባለች እጅ ወጡ።
አንተም በመልእክተኞችህ በኩል እንዲህ ብለህ እግዚአብሔርን ተገዳደርኸው፦ በሰረገላዬ ብዛት ወደ ተራሮች ከፍታ፥ ወደ ሊባኖስ ራስ ወጥቻለሁ፤ ረዣዥሞቹንም ዝግባዎች፥ የተመረጡትንም ጥዶች እቈርጣለሁ፤ ወደ ከፍታውም ዳርቻ ወደ ዱሩ እገባለሁ፤
እግዚአብሔርም ሲሣራን፥ ሰረገሎቹንም ሁሉ፥ ሠራዊቱንም ሁሉ ከባርቅ ፊት በሰይፍ ስለት አስደነገጣቸው፤ ሲሣራም ከሰረገላው ወርዶ በእግሩ ሸሸ።
የእስራኤልም ልጆች ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፤ ዘጠኝ መቶ የብረት ሰረገሎች ነበሩትና፥ የእስራኤልንም ልጆች ሃያ ዓመት እጅግ ያስጨንቃቸው ነበር።