ዘፀአት 12:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአንድ ቤትም ይበላ፤ ከሥጋውም አንዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታውጡ፤ አጥንቱንም አትስበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ምግቡ በአንድ ቤት ውስጥ መበላት አለበት፤ ምንም ሥጋ ከቤት እንዳይወጣ፤ ምንም ዐጥንት እንዳትሰብሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአንድ ቤት ይበላ፤ ከሥጋውም አንዳች ከቤት ወደ ውጭ አይውጣ፤ አጥንቱንም አትስበሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምግቡ በሙሉ በዚያው በተዘጋጀበት ቤት ውስጥ መበላት ስላለበት ወደ ውጪ አይውጣ፤ ከጠቦቱም አጥንቶቹን አትስበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአንድ ቤትም ይበላ፤ ከሥጋውም አንዳች ከቤት ወደ ሜዳ አታውጡ፤ አጥንቱንም አትስበሩ። |
አካል አንድ እንደ ሆነ ብዙ የአካል ክፍሎችም እንደ አሉበት፥ ነገር ግን የአካል ክፍሎች ሁሉ ብዙዎች ሳሉ አንድ አካል እንደ ሆኑ ክርስቶስ ደግሞ እንዲሁ ነው፤