ኤፌሶን 2:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሚመካም እንዳይኖር በምግባራችን አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ማንም እንዳይመካ በሥራ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማንም እንዳይመካ ከሥራ የመጣም አይደለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ማንም ሰው እንዳይመካ፥ የመዳን ጸጋ የተገኘው በሥራ አይደለም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማንም እንዳይመካ ከሥራ አይደለም። |
ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፤ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ፥ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን፤