ሙሴም በዚያች ቀን ይህችን መዝሙር ጻፋት፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተማራት፤ ሙሴም ገባ እርሱና የነዌ ልጅ ኢያሱም የዚህችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።
ሙሴም ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ጋራ መጥቶ የዚህን መዝሙር ቃሎች በሕዝቡ ጆሮ ተናገረ።
ሙሴም ከነዌ ልጅ ከኢያሱ ጋር የዚህን መዝሙር ቃሎች በሕዝቡ ጆሮ ተናገረ።
ሙሴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ሕዝቡ እንደሚሰማ አድርገው ይህን መዝሙር አነበቡ።
ሙሴም የነዌም ልጅ ኢያሱ የዚህችን መዝሙር ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።
ምድሪቱን ይሰልሉ ዘንድ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስሞች እነዚህ ናቸው። ሙሴም የነዌን ልጅ አውሴን ኢያሱ ብሎ ጠራው።
ከኤፍሬም ነገድ የነዌ ልጅ አውሴ፤
ሙሴም በዚያ ቀን ይህችን መዝሙር ጻፈ፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተማራት።
ሙሴም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚህችን መዝሙር ቃሎች እስከ መጨረሻው ድረስ ተናገረ።
ሙሴም ይህን ቃል ሁሉ ለእስራኤል ሁሉ ተናግሮ ፈጸመ።