ዘዳግም 31:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሙሴም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚህችን መዝሙር ቃሎች እስከ መጨረሻው ድረስ ተናገረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሙሴም የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ፣ ለተሰበሰበው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሯቸው እንዲህ ሲል አሰማ፦ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሙሴም የዚህን መዝሙር ቃል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ፥ ለተሰበሰበው የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ በጆሮአቸው እንዲህ ሲል አሰማ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሙሴ በመላው የእስራኤል ጉባኤ ፊት የዚህን መዝሙር ቃሎች ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ አነበበ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሙሴም በእስራኤል ጉባኤ ሁሉ ጆሮ የዚህች መዝሙር ቃሎች እስኪፈጸሙ ድረስ ተናገረ። |
የተናገርሁት ከእኔ የሆነ አይደለምና፤ ነገር ግን የላከኝ አብ እንድናገር፥ እንዲህም እንድል እርሱ ትእዛዝን ሰጠኝ።
ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንድትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ፈቀቅ እንድትሉ አውቃለሁና። በእጃችሁም ሥራ ታስቈጡት ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስላደረጋችሁ፥ በኋለኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገኛችኋል።”
ሙሴም በዚያች ቀን ይህችን መዝሙር ጻፋት፤ ለእስራኤልም ልጆች አስተማራት፤ ሙሴም ገባ እርሱና የነዌ ልጅ ኢያሱም የዚህችን ሕግ ቃሎች ሁሉ በሕዝቡ ጆሮ ተናገሩ።
እነሆ፥ እናንተ ገብታችሁ በምትወርሱአት ምድር ውስጥ እንዲህ ታደርጉ ዘንድ አምላኬ እግዚአብሔር እንዳዘዘኝ ሥርዐትና ፍርድን አሳየኋችሁ።