ዘዳግም 25:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ግርፋቱም አርባ ይሁን፤ ከዚህ በላይ ጨምሮ ብዙ ግርፋት ቢገርፈው ወንድምህ በፊትህ ነውረኛ ይሆናልና ከዚህ በላይ አይጨመርበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሆኖም ግርፋቱ ከአርባ የሚበልጥ አይሁን፤ ከዚህ ካለፈ ግን፣ ወንድምህ በፊትህ የተዋረደ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም ግርፋቱ ከአርባ የሚበልጥ አይሁን፤ ከዚህ ካለፈ ግን፥ ወንድምህ በፊትህ የተዋረደ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስከ አርባ ጅራፍ ሊገርፈው ይችላል፤ ከአርባ ግን መብለጥ የለበትም፤ ከዚያ በላይ ቢገረፍ ወገንህ በፊትህ የተዋረደ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ግርፋቱም አርባ ይሁን፤ ከዚህ በላይ ጨምሮ ብዙ ግርፋት ቢገርፈው ወንድምህ በፊትህ ነውረኛ ይሆናልና ከዚህ በላይ አይጨመርበት። |