እነርሱንም ተቈጣኋቸው፤ ረገምኋቸውም፤ ከእነርሱም ዐያሌዎቹን መታሁ፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ፤ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፥ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።
ዘዳግም 25:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በደለኛውም መገረፍ ቢገባው እንዲገረፍ ፈራጁ በፊቱ በምድር ላይ ያጋድመው፤ የግርፋቱም ቍጥር እንደ ኀጢአቱ መጠን ይሁን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ፣ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፤ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በደለኛው ሰው መገረፍ የሚገባው ሆኖ ከተገኘ ዳኛው መሬት ላይ ያጋድመው፤ ለጥፋቱ ተመጣጣኝ የሆነ ግርፋት እርሱ ባለበት ይገረፍ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በደል የፈጸመው ሰው በግርፋት እንዲቀጣ ቢያስፈልግ፥ በደረቱ መሬት ላይ አስተኝተው ጀርባውን እንዲገርፉት ዳኛው ይዘዝ፤ የሚገረፈውም ዳኛው ባለበትና የግርፋቱም ቊጥር የሚወሰነው ወንጀለኛው በሠራው በደል መጠን ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በደለኛውም መገረፍ ቢገባው እንዲገረፍ ፈራጁ በፊቱ በምድር ላይ ያጋድመው፤ የግርፋቱም ቁጥር እንደ ኃጢአቱ መጠን ይሁን። |
እነርሱንም ተቈጣኋቸው፤ ረገምኋቸውም፤ ከእነርሱም ዐያሌዎቹን መታሁ፤ ጠጕራቸውንም ነጨሁ፤ እንዲህም ብዬ በእግዚአብሔር አማልኋቸው፥ “ሴቶች ልጆቻችሁን ለወንዶች ልጆቻቸው አትስጡ፤ ሴቶች ልጆቻቸውንም ለወንዶች ልጆቻችሁ አትውሰዱ።
ጳውሎስም መልሶ፥ “አንተ የተለሰነ ግድግዳ በሕግ ልትፈርድብኝ ተቀምጠህ ሳለ ያለ ሕግ እመታ ዘንድ ታዝዛለህን? እግዚአብሔር በቍጣው መቅሠፍት ይመታሃል” አለው።
እሺም አሰኛቸው፤ ሐዋርያትንም ጠርተው ገረፉአቸው፤ እንግዲህ ወዲህም በኢየሱስ ስም እንዳያስተምሩ ገሥጸው ተዉአቸው።
ኀጢአት አድርጋችሁ ስትጎሰሙ ብትታገሡ፥ ምን ክብር አለበት? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራን ስትቀበሉ ብትታገሡ፥ ይህ ነገር በእግዚአብሔር ዘንድ ምስጋና ይገባዋል።