La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 19:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ባለ ደሙ ነፍሰ ገዳ​ዩን በልቡ ተና​ድዶ እን​ዳ​ያ​ሳ​ድ​ደው መን​ገ​ዱም ሩቅ ስለ​ሆነ አግ​ኝቶ እን​ዳ​ይ​ገ​ድ​ለው፥ አስ​ቀ​ድሞ ጠላቱ አል​ነ​በ​ረ​ምና ሞት አይ​ገ​ባ​ውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አለዚያ በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፣ መንገዱ ረዥም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አለበለዚያ በተንኰል ሳይሆን ድንገት ሳያስበው ባልንጀራውን ቢገድል፥ መንገዱ ረጅም ከሆነ ደም ተበቃዩ በንዴት ተከታትሎ ይደርስበትና፥ መገደል የማይገባውን ሰው ሊገድል ይችላል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያለው የመጠለያ ከተማ፥ ርቀቱ ቶሎ የማይደረስበት ቢሆን ግን፥ ደሙን ለመበቀል መብት ያለው የሟቹ ዘመድ አባሮ ይዞ በደል የሌለበትን ያን ሰው በቊጣ ሊገድለው ይችላል፤ በእርግጥም ያ ሰው ጠላቱ ያልሆነውን ሰው የገደለው በአጋጣሚ ነበር።

Ver Capítulo



ዘዳግም 19:6
7 Referencias Cruzadas  

እነ​ሆም፥ ዘመ​ዶች ሁሉ በባ​ሪ​ያህ ላይ ተነሡ፤ ስለ ገደ​ለው ስለ ወን​ድሙ ነፍስ እን​ገ​ድ​ለው ዘንድ ወን​ድ​ሙን የገ​ደ​ለ​ውን አውጪ አሉኝ፤ እን​ዲ​ሁም ደግሞ ለባሌ ስምና ዘር በም​ድር ላይ እን​ዳ​ይ​ቀር ወራ​ሹን የቀ​ረ​ውን መብ​ራ​ቴን ያጠ​ፋሉ፤”


ነፍሰ ገዳዩ በማ​ኅ​በሩ ፊት ለፍ​ርድ እስ​ከ​ሚ​ቆም ድረስ እን​ዳ​ይ​ሞት፥ ከተ​ሞቹ ከደም ተበ​ቃይ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች ይሁ​ኑ​ላ​ችሁ።


ሰው ከባ​ል​ን​ጀ​ራው ጋር እን​ጨት ሊለ​ቅም ወደ ዱር ቢሄድ፥ ዛፉ​ንም ሲቈ​ርጥ ምሳሩ ከእጁ ቢወ​ድቅ፥ ብረ​ቱም ከእ​ጄ​ታው ቢወ​ልቅ፥ በባ​ል​ን​ጀ​ራ​ውም ላይ ቢወ​ድ​ቅና ቢገ​ድ​ለው፥ ከእ​ነ​ዚህ ከተ​ሞች በአ​ን​ዲቱ ተማ​ጥኖ በሕ​ይ​ወት ይኖ​ራል፤


ስለ​ዚህ እኔ፦ ለአ​ንተ ሦስት ከተ​ሞ​ችን ለይ ብዬ አዝ​ዤ​ሃ​ለሁ።


“ማንም ሰው ለሞት የሚ​ያ​በ​ቃ​ውን ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እን​ዲ​ሞ​ትም ቢፈ​ረ​ድ​በት፥ በእ​ን​ጨ​ትም ላይ ብት​ሰ​ቅ​ለው፥


ባለ ደሙ ቢያ​ሳ​ድ​ደው፥ አስ​ቀ​ድሞ ሳይ​ጠ​ላው ባል​ን​ጀ​ራ​ውን በስ​ሕ​ተት ስለ ገደ​ለው ነፍሰ ገዳ​ዩን በእጁ አሳ​ል​ፈው አይ​ስ​ጡት።