ዘዳግም 19:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዐይንህም አትራራለት፤ ነፍስ በነፍስ፥ ዐይን በዐይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር ይመለሳል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ርኅራኄ አታድርግ፤ ሕይወት በሕይወት፣ ዐይን በዐይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር ይመለስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓይንህም አትራራለት፥ ሕይወት በሕይወት፥ ዐይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ ይመለስ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእንደዚህ ያለው ክፉ ነገር ላይ ሁሉ ምንም ዐይነት ምሕረት አይኑርህ፤ የቅጣቱም አፈጻጸም ሕይወት ያጠፋ፥ ሕይወቱ እንዲጠፋ፤ ዐይን ያጠፋ፥ ዐይኑ እንዲጠፋ፤ ጥርስ ያወለቀ፥ ጥርሱ እንዲወልቅ፤ እጅ የቈረጠ፥ እጁ እንዲቈረጥ፤ እግርም የሰበረ፥ እግሩ እንዲሰበር በማድረግ ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓይንህም አትራራለት፤ ነፍስ በነፍስ፥ ዓይን በዓይን፥ ጥርስ በጥርስ፥ እጅ በእጅ፥ እግር በእግር፥ ይመለሳል። |