ዘዳግም 14:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእንስሶች ሰኰናው የተሰነጠቀውን፥ ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን፥ የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፣ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳውን ማንኛውንም እንስሳ ብላ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰኰናው ስንጥቅ የሆነውን፥ ለሁለት የተከፈለውንና የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአጠቃላይም ሰኮናቸው የተከፈለና የሚያመሰኩ እንስሶችን ትበላለህ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእንስሶች ሰኮናው የተሰነጠቀውን፥ ጥፍሩም ከሁለት የተከፈለውን፥ የሚያመሰኳውንም እንስሳ ሁሉ ትበላለህ። |
ስለዚህም “ከመካከላቸው ተለይታችሁ ውጡ፤ ከእነርሱም ተለዩ፤ ወደ ርኩሳንም አትቅረቡ፥ እኔም እቀበላችኋለሁ።
ነገር ግን ከሚያመሰኩ ወይም ሰኰናቸው ከተሰነጠቀ እነዚህን አትበሉም፤ ግመልን፥ ሽኮኮን፥ ጥንቸልን አትበሉም፤ ያመሰኳሉና፥ ነገር ግን ሰኰናቸው አልተሰነጠቀምና እነዚህ ለእናንተ ርኩሳን ናቸው።