የግዞት ቤቱ ጠባቂዎች አለቃም በግዞት ቤት የሚደረገውን ሁሉ ምንም አያውቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮሴፍ ትቶለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ ያቀናለት ነበር።
አሞጽ 5:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን ፈልጉ፤ ክፉውንም አይደለም፤ እንዲሁ እናንተ እንደ ተናገራችሁ ሁሉን የሚችል እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕይወት ትኖሩ ዘንድ፣ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ ከዚያ በኋላ እንደ ተናገራችሁት፣ የሰራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕይወት እንድትኖሩ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፤ እንዲሁም እናንተ እንደ ተናገራችሁት የሠራዊት አምላክ ጌታ ከእናንተ ጋር ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉ ነገር አታድርጉ፤ ይህን ብታደርጉ ልክ እናንተ እንደምትሉት የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሕይወት ትኖሩ ዘንድ መልካሙን እንጂ ክፉውን አትፈልጉ፥ እንዲሁም እናንተ እንደ ተናገራችሁ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሆናል። |
የግዞት ቤቱ ጠባቂዎች አለቃም በግዞት ቤት የሚደረገውን ሁሉ ምንም አያውቅም ነበር፤ ሁሉን ለዮሴፍ ትቶለት ነበር፤ እግዚአብሔርም ከእርሱ ጋር ነበረና፤ የሚያደርገውንም ሁሉ እግዚአብሔር በእጁ ያቀናለት ነበር።
ዳዊትም ልጁን ሰሎሞንን፥ “ጠንክር፤ ሰው ሁን፤ አይዞህ፥ አድርገውም፤ አምላኬ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና አትፍራ፤ አትደንግጥም፤ ለእግዚአብሔርም ቤት አገልግሎት የሚሆነውን ሥራ ሁሉ እስክትፈጽም ድረስ እርሱ አይተውህም፤ አይጥልህምም። እነሆ፥ የእግዚአብሔር ቤት ሕንጻ ምሳሌ፥ የአደባባዩ፥ የቤተ መዛግብቱ፥ የሰገነቱ፥ የውስጡ ቤተ መዛግብት፥ የስርየት ቤቱና፥ የእግዚአብሔር ቤት ምሳሌ።
እርሱም ንጉሡን አሳን፥ የይሁዳንና የብንያምን ሕዝብ ሁሉ ሊገናኝ ወጣ፤ እንዲህም አለ፥ “አሳ ይሁዳና ብንያም ሁሉ ሆይ፥ ስሙኝ፤ እናንተ ከእግዚአብሔር ጋር ብትሆኑ እርሱ ከእናንተ ጋር ይሆናል፤ ብትፈልጉትም ይገኝላችኋል፤ ብትተዉት ግን ይተዋችኋል።
እግዚአብሔርም ሙሴን ተናገረው፤ እንዲህ ሲል፥ “በእውነት እኔ ከአንተ ጋር እሆናለሁ፤ እኔም እንደ ላክሁህ ይህ ለአንተ ምልክት ይሆንሃል፤ ሕዝቡን ከግብፅ በአወጣህ ጊዜ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን ታመልካላችሁ” አለው።
ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፤ በረከትንም ብሉ፤ ሰውነታችሁም በበረከት ደስ ይበለው።
ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
በዮሴፍ ቤት እሳት እንዳትቃጠል፥ እንዳትበላቸውም የእስራኤልንም ቤት እሳት የሚያጠፋላቸው እንዳያጡ እግዚአብሔርን ፈልጉ፤ በሕይወትም ትኖራላችሁ።
አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቶችዋም በዋጋ ያስተምራሉ፥ ነቢያቶችዋም በገንዘብ ያምዋርታሉ፥ ከዚህም ጋር፦ እግዚአብሔር በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር ምንም አይመጣብንም እያሉ በእግዚአብሔር ይታመናሉ።
ሰው ሆይ፥ መልካሙን ነግሮሃል፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ፥ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፥ ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሄድ ዘንድ አይደለምን?
እናንተ ፍርዱን የጠበቃችሁ የምድር ትሑታን ሁሉ፥ እግዚአብሔርን ፈልጉ፣ ጽድቅንም ፈልጉ፥ ትሕትናንም ፈልጉ፣ ምናልባት በእግዚአብሔር ቍጣ ቀን ትሰወሩ ይሆናል።
በሙሴና በአሮን ላይ ተነሡ፤ “ለእናንተ ይበቃችኋል፤ ማኅበሩ ሁሉ እያንዳንዳቸው ቅዱሳን ናቸውና፥ እግዚአብሔርም በመካከላቸው ነውና፤ በእግዚአብሔርስ ጉባኤ ላይ ለምን ትታበያላችሁ?” አሉአቸው።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
እነሆ አዝዝሃለሁ፤ በምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ በርታ፤ አትፍራ፥ አትደንግጥም።”