ከእርሱም ጋር የነበሩት ሰዎች ድምፅ እየሰሙ ማንንም ሳያዩ ተደንቀው ቆሙ።
ከሳውል ጋራ ይጓዙ የነበሩትም ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንንም ባላዩ ጊዜ፣ አፋቸውን ይዘው ቆሙ።
ከእርሱም ጋር በመንገድ የሄዱ ሰዎች ድምፁን እየሰሙ ማንን ግን ሳያዩ እንደ ዲዳዎች ቁሙ።
ከሳውል ጋር ይሄዱ የነበሩ ሰዎች ድምፅ እየሰሙ ማንንም ባለማየታቸው የሚናገሩትን አጥተው፥ ዝም ብለው ቆሙ።
በዚያ ቆመው ይሰሙ የነበሩ ሕዝብ ግን “ነጐድጓድ ነው” አሉ፤ “መልአክ ተናገረው” ያሉም አሉ።
አብረውኝ የነበሩትም መብረቁን አይተው ደነገጡ፤ ነገር ግን ይናገረኝ የነበረውን ቃል አልሰሙም።