ሐዋርያት ሥራ 9:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም እየፈራና እየተንቀጠቀጠ፥ “አቤቱ፥ ምን እንዳደርግ ትሻለህ?” አለው፤ ጌታም፥ “ተነሣና ወደ ከተማ ግባ፤ በዚያም ልታደርገው የሚገባህን ይነግሩሃል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ተነሣና ወደ ከተማዪቱ ግባ፤ ማድረግ የሚገባህም ይነገርሃል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ “ጌታ ሆይ! ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል፤” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁን ግን ተነሥና ወደ ከተማ ግባ፤ ልታደርገው የሚገባህም እዚያ ይነገርሃል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እየተንቀጠቀጠና እየተደነቀ፦ “ጌታ ሆይ፥ ምን አደርግ ዘንድ ትወዳለህ?” አለው። ጌታም፦ “ተነሥተህ ወደ ከተማ ግባና ታደርገው ዘንድ የሚያስፈልግህን ይነግሩሃል” አለው። |
ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር፤ “ወደ የዋሁና ወደ ጸጥተኛው፥ ከቃሌም የተነሣ ወደሚንቀጠቀጥ ሰው ከአልሆነ በቀር ወደ ማን እመለከታለሁ?
እኔ ሰምቻለሁ፥ ልቤም ደነገጠብኝ፣ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፣ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፣ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ፣ በሚያስጨንቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።
እነርሱም፥ “የመቶ አለቃ ቆርኔሌዎስ እግዚአብሔርን የሚፈራ ጻድቅ ሰው ነው፤ በአይሁድም ወገኖች ሁሉ የተመሰከረለት ነው፤ ቅዱስ መልአክ ተገልጦ አንተን ወደ ቤቱ እንዲጠራህ የምታስተምረውንም እንዲሰማ አዝዞታል፤” አሉት።
አሁንም ወደ ኢዮጴ ከተማ ላክና በባሕር አቅራቢያ ባለችው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ቤት የሚኖረውን ጴጥሮስ የተባለውን ስምዖንን ይጥሩልህ፤ እርሱ መጥቶ የምትድንበትን ይነግርሃል።
እርሱም ቤቱ በባሕር አጠገብ ባለው በቍርበት ፋቂው በስምዖን ቤት እንግድነት ተቀምጦአል። ልታደርገው የሚገባህን እርሱ ይነግርሃል።”
ይህንም በሰሙ ጊዜ ልባቸው ተከፈተ፤ ጴጥሮስንና ወንድሞቹ ሐዋርያትንም፥ “ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምን እናድርግ?” አሏቸው።
‘አቤቱ፥ ጌታዬ ምን ላድርግ?’ አልሁ፤ ጌታም፦ ‘ተነሥና ወደ ደማስቆ ሂድ፤ ልታደርገው የሚገባህንም ሁሉ በዚያ ይነግሩሃል’ አለኝ።
ነገር ግን ተነሣና በእግርህ ቁም፤ እኔን ባየህበትና ወደፊትም በምታይበት ነገር አገልጋይና ምስክር አድርጌ ልሾምህ ስለዚህ ተገልጬልሃለሁና።
ሳውልም፥ “አቤቱ፥ አንተ ማነህ?” አለው፤ እርሱም፥ “አንተ የምታሳድደኝ የናዝሬቱ ኢየሱስ ነኝ፤ በሾለ ብረት ላይ ብትቆም ለአንተ ይብስሃል” አለው።
የእግዚአብሔርን ጽድቅ አያውቁአትምና በራሳቸውም ጽድቅ ጸንተው ሊኖሩ ወደዱ፤ ለእግዚአብሔር ጽድቅ ግን መገዛት ተሳናቸው።
አሁንም ወንድሞች ሆይ፥ ዘወትር እንደምትሰሙኝ ሳለሁ ብቻ ሳይሆን፥ ሳልኖርም በፍርሀትና በመንቀጥቀጥ ሆናችሁ ለድኅነታችሁ ሥሩ።