ገመዶችሽ ተበጥሰዋል፤ ጥንካሬ የላቸውምና፤ ደቀልሽ ዘመመ፤ ሸራውንም መዘርጋት አልቻለም፤ እስከሚያዝም ድረስ አላማውን አልተሸከመም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ተከፈለ፤ ብዙ አንካሶች እንኳ ምርኮውን ማረኩ።
ሐዋርያት ሥራ 27:40 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መልሕቁንም ፈትተው በባሕር ላይ ጣሉት፤ የሚያቆሙበትንም አመቻችተው እንደ ነፋሱ አነፋፈስ መጠን ትንሹን ሸራ ሰቀሉ፤ ወደ ባሕሩ ዳርቻም ሄድን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም መልሕቆቹን ቈርጠው ባሕር ውስጥ ጥለው ሄዱ፤ የመቅዘፊያውንም ገመድ በዚያው ጊዜ ፈቱ፤ የፊተኛውንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ አቀኑ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልሕቆቹንም ፈትተው በባሕር ተዉአቸው፤ ያን ጊዜም የመቅዘፊያውን ማሠሪያ ፈቱት፤ ታናሹንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ዳር አቅንተው ይሄዱ ዘንድ ጀመሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልሕቆቹን ፈተው በባሕር ውስጥ ለቀቁአቸው፤ በዚያኑ ጊዜም የመቅዘፊያውን ገመዶች ፈቱ፤ ከዚህ በኩል ያለውን ሸራ ወደ ነፋሱ ከፍ አድርገው ወደ ባሕሩ ዳርቻ ለመውጣት ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልሕቆቹንም ፈትተው በባሕር ተዉአቸው፥ ያን ጊዜም የመቅዘፊያውን ማሠሪያ ፈቱት፤ ታናሹንም ሸራ ለነፋስ ከፍ አድርገው ወደ ዳር አቅንተው ይሄዱ ዘንድ ጀመሩ። |
ገመዶችሽ ተበጥሰዋል፤ ጥንካሬ የላቸውምና፤ ደቀልሽ ዘመመ፤ ሸራውንም መዘርጋት አልቻለም፤ እስከሚያዝም ድረስ አላማውን አልተሸከመም። በዚያን ጊዜ የብዙ ምርኮ ተከፈለ፤ ብዙ አንካሶች እንኳ ምርኮውን ማረኩ።
በገሊላ ባሕር አጠገብ ሲመላለስም ሁለት ወንድማማች ጴጥሮስ የሚሉትን ስምዖንን ወንድሙንም እንድርያስን መረባቸውን ወደ ባሕር ሲጥሉ አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ነበሩና።
ከዚህ በኋላ ተጋግዘን በገመድ አጠናከርናት፤ ከዚህም ቀጥሎ ቀዛፊዎች ወደ ጥልቁ ባሕር እንዳይወድቁ በፈሩ ጊዜ ሸራውን አወረዱ፤እንዲሁም እንድንሄድ አደረግን።
መርከቢቱም በሁለት ታላላቅ ድንጋዮች መካከል ተቀረቀረች፤ ባሕሩም ጥልቅ ነበረ። ከወደፊቷም ተያዘች፤ አልተንቀሳቀሰችምም፤ ከሞገዱም የተነሣ በስተኋላ በኩል ጎንዋን ተሰብራ ተጐረደች፤ ቀዛፊዎችም ወደፊት ሊገፉአት አልቻሉም።