La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 21:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ከእ​ነ​ር​ሱም ከተ​ለ​የን በኋላ እኛ በመ​ር​ከብ ተሳ​ፍ​ረን፥ መን​ገ​ዳ​ች​ን​ንም አቅ​ን​ተን ወደ ቆስ መጣን፤ በበ​ነ​ጋ​ውም ወደ ሮዶስ፥ ከዚ​ያም ወደ ጳጥራ ገባን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከእነርሱ ከተለየን በኋላ ቀጥታ በመርከብ ወደ ቆስ ተጓዝን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ፣ ከዚያም ወደ ጳጥራ አመራን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእነርሱም ተለይተን ተነሣን፤ በቀጥታም ሄደን ወደ ቆስ በነገውም ወደ ሩድ ከዚያም ወደ ጳጥራ መጣን፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከእነርሱ ከተለየን በኋላ በመርከብ ተሳፈርንና በቀጥታ ቆስ ወደምትባል ደሴት ሄድን፤ በማግስቱም ወደ ሩድ ደሴት ደረስን፤ ከዚያም ወደ ጳጥራ ከተማ ሄድን።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ከእነርሱም ተለይተን ተነሣን፤ በቀጥታም ሄደን ወደ ቆስ በነገውም ወደ ሩድ ከዚያም ወደ ጳጥራ መጣን፤

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 21:1
8 Referencias Cruzadas  

ትም​ህ​ር​ቱ​ንም ከፈ​ጸመ በኋላ ስም​ዖ​ንን፥ “ወደ ጥልቁ ባሕር ፈቀቅ በል፤ መረ​ቦ​ቻ​ች​ሁ​ንም ለማ​ጥ​መድ ጣሉ” አለው።


ከዕ​ለ​ታት በአ​ን​ዲት ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ እርሱ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ ወጣና፥ “ኑ ወደ ባሕሩ ማዶ እን​ሻ​ገር” አላ​ቸው እነ​ር​ሱም ሄዱ።


በተ​ነ​ሣ​ንም ጊዜ ወደ እስያ በም​ት​ሄድ በአ​ድ​ራ​ማ​ጢስ መር​ከብ ተሳ​ፈ​ርን፤ የተ​ሰ​ሎ​ንቄ ሀገር ሰው የሚ​ሆን መቄ​ዶ​ን​ያ​ዊው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስም አብ​ሮን ሄደ።


ከዚ​ያም ወጥ​ተን ነፋስ ፊት ለፊት ነበ​ርና በቆ​ጵ​ሮስ በኩል ዐለ​ፍን።


እኛ ግን ወንድሞች ሆይ! በልብ ያይደለ ፊት ለፊት ለጥቂት ጊዜ አጥተናችሁ፥ በብዙ ናፍቆት ፊታችሁን ለማየት እጅግ ሞከርን፤