Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሉቃስ 8:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ከዕ​ለ​ታት በአ​ን​ዲት ቀንም እን​ዲህ ሆነ፤ እርሱ ከደቀ መዛ​ሙ​ርቱ ጋር ወደ ታንኳ ወጣና፥ “ኑ ወደ ባሕሩ ማዶ እን​ሻ​ገር” አላ​ቸው እነ​ር​ሱም ሄዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከዕለታቱ በአንድ ቀን፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ጀልባ ላይ ወጣ፤ ኢየሱስም፤ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው፤ ከዚያም ጕዞ ቀጠሉ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ከዕለታቱም በአንዱ ቀንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ “ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር፤” አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 አንድ ቀን ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በጀልባ ተሳፈረና “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር፤” አላቸው፤ እነርሱም ለመሄድ ተነሡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ከዕለታቱም በአንዱ እርሱ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ወደ ታንኳ ገብቶ፦ ወደ ባሕር ማዶ እንሻገር አላቸው፤ ተነሡም።

Ver Capítulo Copiar




ሉቃስ 8:22
12 Referencias Cruzadas  

ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳ ገብተው ወደ ማዶ ወደ ቤተ ሳይዳ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።


ሲሄ​ዱም አን​ቀ​ላፋ፤ በባ​ሕ​ሩም ላይ ዐውሎ ነፋስ መጣ፤ ውኃ​ዉም ታን​ኳ​ቸ​ውን ሞላው፤ እነ​ር​ሱም ተጨ​ነቁ።


ብዙ ሰዎ​ችም በእ​ርሱ ዘንድ ነበሩ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ይሰሙ ነበር፤ እርሱ ግን በጌ​ን​ሴ​ሬጥ ባሕር ወደብ ቁሞ ነበር።


ትቶአቸውም እንደ ገና ወደ ታንኳይቱ ገብቶ ወደ ማዶ ሄደ።


ወዲያውም ሕዝቡን ሲያሰናብት ሳለ፥ ደቀ መዛሙርቱ በታንኳይቱ ገብተው ወደ ማዶ እንዲቀድሙት ግድ አላቸው።


ከዚህ በኋላ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ወደ ገሊላ ባሕር ማዶ ወደ ጥብ​ር​ያ​ዶስ ሄደ።


ኢየሱስም ደግሞ በታንኳይቱ ወደ ማዶ ከተሻገረ በኋላ ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ ተሰበሰቡ፤ በባሕርም አጠገብ ነበረ።


ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ።


እነ​ዚያ አጋ​ን​ን​ትም ከዚያ ሰው ላይ ወጥ​ተው ወደ እሪ​ያ​ዎች ገቡ፤ የእ​ሪ​ያ​ዎ​ችም መንጋ አብ​ደው ከገ​ደሉ ወደ ባሕር ጠል​ቀው ሞቱ።


በተ​ነ​ሣ​ንም ጊዜ ወደ እስያ በም​ት​ሄድ በአ​ድ​ራ​ማ​ጢስ መር​ከብ ተሳ​ፈ​ርን፤ የተ​ሰ​ሎ​ንቄ ሀገር ሰው የሚ​ሆን መቄ​ዶ​ን​ያ​ዊው አር​ስ​ጥ​ሮ​ኮ​ስም አብ​ሮን ሄደ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios