La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 7:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በኋ​ላ​ቸ​ውም እስከ ዮር​ዳ​ኖስ ድረስ ተከ​ት​ለ​ዋ​ቸው ሄዱ፤ እነ​ሆም፥ ሶር​ያ​ው​ያን ሲሸሹ የጣ​ሉት ልብ​ስና ዕቃ መን​ገ​ዱን ሁሉ ሞልቶ አገኙ። እነ​ዚያ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችም ተመ​ል​ሰው ለእ​ስ​ራ​ኤል ንጉሥ ነገ​ሩት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነርሱም እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ተከተሏቸው። ሶርያውያን በጥድፊያ ሲሸሹ፣ የጣሉትንም ልብስና ዕቃ በየመንገዱ ላይ ተበታትኖ አገኙ፤ መልእክተኞቹም ተመልሰው ይህንኑ ለንጉሡ ነገሩት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው እስከ ዮርዳኖስ ወንዝ ድረስ ዘልቀው ሄዱ፤ በየመንገዱም ሶርያውያን ሲሸሹ ጥለውት የሄዱትን ልብስና መሣሪያ ሁሉ አዩ፤ ከዚያም በኋላ ተመልሰው መጥተው ይህን ሁሉ ለንጉሡ ነገሩ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በኋላቸው እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ሄዱ፤ እነሆም፥ ሶርያውያን ሲሸሹ የጣሉት ልብስና ዕቃ መንገዱን ሁሉ ሞልቶ ነበር። መልእክተኞችም ተመልሰው ለንጉሡ ነገሩት።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 7:15
14 Referencias Cruzadas  

ሁለት ፈረ​ሰ​ኞ​ች​ንም ወሰዱ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ንጉ​ሥም፥ “ሄዳ​ችሁ እዩ” ብሎ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን ንጉሥ ይከ​ተ​ሉት ዘንድ ላከ።


ሕዝ​ቡም ወጥቶ የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን ሰፈር በዘ​በዘ፤ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቃል አንድ መስ​ፈ​ሪያ መል​ካም ዱቄት በአ​ንድ ሰቅል፥ ሁለት መስ​ፈ​ሪያ ገብ​ስም በአ​ንድ ሰቅል ተሸ​መተ።


ሰይ​ጣ​ንም መልሶ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፥ “ቍር​በት ስለ ቍር​በት ነው፤ ሰው ያለ​ውን ሁሉ ስለ ሕይ​ወቱ ይሰ​ጣል።


ለመ​ፈ​ለግ ጊዜ አለው፥ ለማ​ጥ​ፋ​ትም ጊዜ አለው፤ ለመ​ጠ​በቅ ጊዜ አለው፥ ለመ​ጣ​ልም ጊዜ አለው፤


በተ​ጐ​በ​ኛ​ች​ሁ​በት ቀን፥ ምን ታደ​ርጉ ይሆን? መከራ ከሩቅ ይመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ልና፥ ለረ​ድ​ኤ​ትስ ወደ ማን ትሸ​ሻ​ላ​ችሁ?


በዚ​ያም ቀን ሰው ይሰ​ግ​ድ​ላ​ቸው ዘንድ ያበ​ጁ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቹን ለፍ​ል​ፈ​ልና ለሌ​ሊት ወፍ ይጥ​ላል።


የአ​ባ​ቱ​ንም ቤት ክብር ሁሉ፥ ልጆ​ቹ​ንም፥ የልጅ ልጆ​ቹ​ንም፥ ከጽዋ ዕቃ ጀምሮ እስከ ማድጋ ዕቃ ድረስ፥ ታና​ና​ሹ​ንና ታላ​ላ​ቁን ሁሉ ይሰ​ቅ​ሉ​በ​ታል።


በዚ​ያም ቀን እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸው እጆ​ቻ​ቸው የሠ​ሩ​አ​ቸ​ውን የብ​ሩ​ንና የወ​ር​ቁን ጣዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውን ይጥ​ላሉ።


የበ​ደ​ላ​ች​ሁ​ትን በደል ሁሉ ከእ​ና​ንተ ጣሉ፤ አዲስ ልብና አዲስ መን​ፈ​ስ​ንም ለእ​ና​ንተ አድ​ርጉ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! ስለ ምን ትሞ​ታ​ላ​ችሁ?


ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል? ወይስ ሰው ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?


እን​ግ​ዲህ እነ​ዚ​ህን የሚ​ያ​ህሉ ምስ​ክ​ሮች እንደ ደመና በዙ​ሪ​ያ​ችን ካሉ​ልን እኛ ደግሞ ሸክ​ምን ሁሉ፥ የኀ​ጢ​አ​ት​ንም ጭን​ቀት ከእኛ አስ​ወ​ግ​ደን፥ በፊ​ታ​ችን ያለ​ውን ሩጫ በት​ዕ​ግ​ሥት እን​ሩጥ።