2 ቆሮንቶስ 7:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጀመሪያ በጻፍሁት መልእክት ባሳዝናችሁም እንኳ አያጸጽተኝም፤ ብጸጸትም፥ እነሆ ያች መልእክት ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘነቻችሁ አያለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመልእክቴ ባሳዝናችሁም በዚህ አልጸጸትም፤ ብጸጸትም እንኳ መልእክቴ ያሳዘናችሁ ለጥቂት ጊዜ እንደ ሆነ ተረድቻለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመልእክቴ ያሳዘንኋችሁ ብሆን እንኳ አልጸጸትም፤ የተጸጸትሁ ብሆን እንኳ፥ ያ መልእክት ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘናችሁ ተረድቻለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በፊት የጻፍኩላችሁ መልእክት ያሳዘናችሁ ቢሆንም እንኳ መልእክቱን በመጻፌ አልጸጸትም፤ ተጸጽቼም ብሆን እንኳ የተጸጸትኩት መልእክቴ ለጥቂት ጊዜ ስላሳዘናችሁ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመልእክቴ ያሳዘንኋችሁ ብሆን እንኳ አልጸጸትም፤ የተጸጸትሁ ብሆን እንኳ፥ ያ መልእክት ጥቂት ጊዜ ብቻ እንዳሳዘናችሁ አያለሁና አሁን ለንስሐ ስላዘናችሁ ደስ ብሎኛል እንጂ ስላዘናችሁ አይደለም፤ |
ሦስተኛ ጊዜም፥ “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን?” አለው፤ ጴጥሮስም ሦስት ጊዜ ትወደኛለህን? ስላለው ተከዘ፤ “ጌታዬ ሆይ፥ አንተ ሁሉን ታውቃለህ፤ እኔም እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ” አለው፤ “እንኪያስ ግልገሎችን ጠብቅ” አለው።
እነሆ፥ ያ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ ያደረጋችሁት ኀዘን ምንም የማታውቁ እስከ መሆን ደርሳችሁ፥ ራሳችሁን በበጎ ሥራና በንጽሕና እስክታጸኑ ድረስ፥ ትጋትንና ክርክርን፥ ቍጣንና ፍርሀትን፥ ናፍቆትንና ቅንዐትን፥ በቀልንም አደረገላችሁ፤
ይህን የጻፍሁላችሁ በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ እንደ ተጋችሁ ይታወቅ ዘንድ ነው እንጂ ስለ በደለና ስለ ተበደለ ሰው አይደለም።
በመምጣቱ ብቻ አይደለም፤ በአጽናናችሁት ማጽናናትም ነው እንጂ፤ ለእኛ እንደምታስቡና እንደምትቀኑ ፍቅራችሁን ነግሮናል፤ ይህንም ሰምቼ ደስታዬ በእናንተ በዛ።
አሁን ግን እኔ ስለ እርሷ በብዙ ደስ ይለኛል፤ ደስታዬም ስለ አዘናችሁ አይደለም፤ ንስሓ ልትገቡ ስለ አዘናችሁ እንጂ፤ ከእናንተ አንዱ ስንኳ እንዳይጠፋ፥ ስለ እግዚአብሔር ብላችሁ አዝናችኋልና።