ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
1 ሳሙኤል 30:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዳዊትም የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ “ኤፉዱን አቅርብልኝ” አለው፤ አብያታርም ኤፉዱን ለዳዊት አቀረበለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ዳዊት የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፣ “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም አመጣለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ዳዊት የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፥ “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም አመጣለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም የአቤሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን “ኤፉዱን አምጣልኝ” አለው፤ አብያታርም ኤፉዱን አመጣለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም የአቢሜሌክን ልጅ ካህኑን አብያታርን፦ ኤፉዱን አቅርብልኝ አለው፥ አብያታርም ኤፋዱን ለዳዊት አቀረበለት። |
ንጉሡም ካህኑን አብያታርን፥ “አንተ ዛሬ የሞት ሰው ነበርህ፤ ነገር ግን የአምላክን የእግዚአብሔርን ታቦት በአባቴ በዳዊት ፊት ስለ ተሸከምህ፥ አባቴም የተቀበለውን መከራ ሁሉ አንተ ስለ ተቀበልህ አልገድልህምና በዓናቶት ወዳለው ወደ እርሻህ ፈጥነህ ሂድ” አለው።
“ልብሰ መትከፉንም ከወርቅ፥ ከሰማያዊና ከሐምራዊ፥ ከተፈተለ ከቀይ ግምጃ በግብረ መርፌ የተሠራ፥ የተለየ የሽመና ሥራ ያድርጉ።
አብያተር ሊቀ ካህናት በነበረ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ቤት እንደ ገባ፥ ከካህናት በቀር መብላት ያልተፈቀደውን የመሥዋዕትን እንጀራ እንደ በላ፥ ከእርሱም ጋር ለነበሩት እንደ ሰጣቸው ከቶ አላነበባችሁምን?” አላቸው።
ሳሙኤልም፦ ያ ሰው እዚህ ይመጣ እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠየቀ፤ እግዚአብሔርም፥ “እነሆ፥ በዕቃ መካከል ተሸሽጎአል” ብሎ መለሰ።
ሳኦልም ከካህኑ ጋር ሲነጋገር በፍልስጥኤማውያን መንደር ግርግርታ እየበዛ ሄደ፤ ሳኦልም ካህኑን፥ “እጅህን መልስ” አለው።