Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፀአት 28:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 “ልብሰ መት​ከ​ፉ​ንም ከወ​ርቅ፥ ከሰ​ማ​ያ​ዊና ከሐ​ም​ራዊ፥ ከተ​ፈ​ተለ ከቀይ ግምጃ በግ​ብረ መርፌ የተ​ሠራ፥ የተ​ለየ የሽ​መና ሥራ ያድ​ርጉ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 “የጥልፍ ዐዋቂዎች ኤፉዱን ከወርቅ፣ ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና በቀጭኑ ከተፈተለ በፍታ ይሥሩት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 “ኤፉዱንም በወርቅ፥ በሰማያዊ፥ በሐምራዊ፥ በቀይ ግምጃና ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም በብልሃት የተሠራ ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 “ኤፉድንም ከሰማያዊ፥ ከሐምራዊ ከቀይ ከፈይ ከወርቅ ምዝምዝና ከጥሩ በፍታ በጥልፍ አስጊጠው ይሥሩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ኤፉዱንም በብልሃት የተሠራ በወርቅና በሰማያዊ በሐምራዊም በቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም ብልህ ሠራተኛ እንደሚሠራ ያድርጉ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 28:6
11 Referencias Cruzadas  

ሰማ​ያ​ዊና ሐም​ራዊ፥ ቀይም ድርብ ግምጃ፥ ጥሩ በፍ​ታም፥


መረ​ግ​ድም፥ ለል​ብሰ እን​ግ​ድ​ዓና ለደ​ረት ኪስ የሚ​ደ​ረግ ፈርጥ።


“ለድ​ን​ኳ​ኑም ከተ​ፈ​ተለ ከጥሩ በፍታ፥ ከሰ​ማ​ያዊ፥ ከሐ​ም​ራ​ዊም፥ ከቀ​ይም ግምጃ ዐሥር መጋ​ረ​ጆ​ችን ሥራ፤ ኪሩ​ቤ​ልም በእ​ነ​ርሱ ላይ ይሁኑ፤ እንደ ሽመና ሥራም በብ​ል​ሃት ትሠ​ራ​ቸ​ዋ​ለህ።


ሁለቱ ወገን አንድ እን​ዲ​ሆን በሁ​ለቱ ጫንቃ ላይ የሚ​ጋ​ጠም ጨርቅ ይሁን።


ልብ​ሶ​ችን ወስ​ደህ ለወ​ን​ድ​ምህ ለአ​ሮን የነጭ ሐር እጀ ጠባብ ቀሚስ፥ ልብሰ መት​ከ​ፍና ልብሰ እን​ግ​ድዓ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ለእ​ር​ሱም ልብሰ እን​ግ​ድ​ዓ​ውን ከል​ብሰ መት​ከፉ ጋር አያ​ይ​ዝ​ለት።


የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ያለ ንጉ​ሥና ያለ አለቃ፥ ያለ መሥ​ዋ​ዕ​ትና ያለ ምሥ​ዋዕ፤ ያለ ካህ​ንና ያለ ራእይ፤ ያለ ኤፉ​ድና ያለ ተራ​ፊም ብዙ ወራት ይቀ​መ​ጣ​ሉና፤


እጀ ጠባ​ብም አለ​በ​ሰው፤ በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም አስ​ታ​ጠ​ቀው፤ የበ​ፍታ ቀሚ​ስም አለ​በ​ሰው፤ ልብሰ መት​ከ​ፍም ደረ​በ​ለት፤ በል​ብሰ መት​ከ​ፉም አሠ​ራር ላይ በብ​ል​ሃት በተ​ጠ​ለፈ ቋድ አስ​ታ​ጠ​ቀ​ውና በእ​ርሱ ላይ አሰ​ረው።


ጌዴ​ዎ​ንም ምስል አድ​ርጎ ሠራው፤ በከ​ተ​ማ​ውም በኤ​ፍ​ራታ አኖ​ረው፤ እስ​ራ​ኤ​ልም ሁሉ ተከ​ትሎ አመ​ነ​ዘ​ረ​በት፤ ለጌ​ዴ​ዎ​ንና ለቤ​ቱም ወጥ​መድ ሆነ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የአ​ቤ​ሜ​ሌክ ልጅ አብ​ያ​ታር ወደ ዳዊት ወደ ቂአላ በኰ​በ​ለለ ጊዜ ኤፉ​ዱን ይዞ ወርዶ ነበር።


ዳዊ​ትም የአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክን ልጅ ካህ​ኑን አብ​ያ​ታ​ርን፥ “ኤፉ​ዱን አቅ​ር​ብ​ልኝ” አለው፤ አብ​ያ​ታ​ርም ኤፉ​ዱን ለዳ​ዊት አቀ​ረ​በ​ለት።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos