ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቤግያ ጋር ወደዚያ ወደ ኬብሮን ወጣ።
1 ሳሙኤል 30:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም ሁለቱ ሚስቶቹ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቤግያ ተማርከው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያም ተማርከው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች ማለትም ኢይዝራኤላዊቷ አሒኖዓምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢጌልም ተማርከው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱ የዳዊት ሚስቶች የኢዝራኤላይቱን አሒኖዓምና የቀርሜሎሳይቱ የናባል ሚስት የነበረችው አቢጌል ተማርከው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም ሁለቱ ሚስቶቹ ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት የነበረችው አቢግያ ተማርከው ነበር። |
ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ከኢይዝራኤላዊቱ ከአኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት ከነበረችው ከአቤግያ ጋር ወደዚያ ወደ ኬብሮን ወጣ።
ሁለትም ሚስቶች ነበሩት፤ የአንዲቱ ስም ሐና፥ የሁለተኛዪቱም ስም ፍናና ነበረ፤ ለፍናናም ልጆች ነበሩአት፤ ለሐና ግን ልጆች አልነበሩአትም።
ዳዊትና ሰዎቹም እያንዳንዳቸው ከነቤተሰቡ ከአንኩስ ጋር በጌት ተቀመጡ፤ ከዳዊትም ጋር ኢይዝራኤላዊቱ አኪናሆምና የቀርሜሎሳዊው የናባል ሚስት አቤግያ ሁለቱ ሚስቶቹ ነበሩ።