አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
1 ሳሙኤል 25:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነርሱም ጋር ሆነን መንጋውን በጠበቅንበት ዘመን ሁሉ በምድረ በዳ ሌሊትና ቀን አጥር ሆነውን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጎቻችንን እየጠበቅን ዐብረናቸው ባሳለፍነው ጊዜ ሁሉ፣ ቀንም ሆነ ሌሊት በዙሪያችን ዐጥር ሆነውን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጎቻችንን እየጠበቅን አብረናቸው ባሳለፍነው ጊዜ ሁሉ፥ ቀንም ሆነ ሌሊት በዙሪያችን አጥር ሆነውን ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንጋዎቻችንን እየጠበቅን በቈየንበት ጊዜ ሁሉ በቀንም ሆነ በሌሊት እነርሱ ለእኛ አጥር ሆነውን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነርሱ ጋር ሆነን መንጋውን በጠበቅንበት ዘመን ሁሉ ሌሊትና ቀን አጥር ሆነውን ነበር። |
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
ስለዚህም በጌታችንና በቤቱ ሁላ ክፉ ነገር እንዲመጣ ተቈርጦአልና፥ እርሱ ክፉ ሰው ስለ ሆነ ማንም ሊናገረው አይችልምና የምታደርጊውን ተመልከቺና ዕወቂ።”