1 ሳሙኤል 2:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዔሊም እጅግ አረጀ፤ ልጆቹም የእስራኤልን ልጆች ያደረጓቸውን፥ በምስክሩ ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉት ሴቶችም ጋር እንደሚተኙ ሰማ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ዔሊ እጅግ አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹም በመላው እስራኤል ያደርጉ የነበረውን፣ በመገናኛውም ድንኳን ደጃፍ ከሚያገለግሉ ሴቶች ጋራ ዝሙት መፈጸማቸውን ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዔሊም እጅግ አረጀ፤ ልጆቹም በእስራኤል ሁሉ ላይ ያደረጉትን ሁሉ፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጅ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደ ተኙ ሰማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነሆ ዔሊ በዕድሜው አርጅቶ ነበር፤ ልጆቹም በእስራኤላውያን ላይ የሚያደርጉት ክፉ ነገርና በድንኳኑ ደጃፍ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደሚያመነዝሩ ሰማ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዔሊም እጅግ አረጀ፥ ልጆቹም በእስራኤል ሁሉ ላይ ያደረጉትን ሁሉ፥ በመገናኛውም ድንኳን ደጅ ከሚያገለግሉት ሴቶች ጋር እንደ ተኙ ሰማ። |
የያዕቆብም ትውልድ እንዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ እርሱም ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላቴና ነበረ፤ ዮሴፍም የክፋታቸውን ወሬ ወደ አባታቸው ወደ እስራኤል ያመጣ ነበር።
ካህናቷም ሕጌን ጣሱ፤ በመቅደሴም መካከል ቅድሳቴን አረከሱ፤ ከርኵሰትም አልራቁም፤ በንጹሕና በርኩስ መካከል ያለውንም ልዩነት አላወቁም፤ ዐይናቸውንም ከሰንበታቴ ሸፈኑ፤ እኔም በመካከላቸው ረከስሁ።
ልጆቹ በእግዚአብሔር ላይ ክፉ እንዳደረጉ ዐውቆ አልገሠጻቸውምና ስለ ልጆቹ ኀጢአት ለዘለዓለም ቤቱን እንደምበቀል አስታውቄዋለሁ።