1 ሳሙኤል 16:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሴይም አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት አሳለፈው፤ እርሱም፥ “ይህን ደግሞ እግዚአብሔር አልመረጠውም” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን፣ “እግዚአብሔር ይህንም አልመረጠውም” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም እሴይ አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት እንዲያልፍ አደረገ፤ ሳሙኤል ግን፥ “ጌታ ይህንንም አልመረጠውም” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እሴይ አቢናዳብ ተብሎ የሚጠራውን ልጁን ወደ ሳሙኤል አመጣለት፤ ሳሙኤል ግን “እግዚአብሔር ይህኛውንም አልመረጠውም” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እሴይም አሚናዳብን ጠርቶ በሳሙኤል ፊት አሳለፈው፥ እርሱም፦ ይህን ደግሞ እግዚአብሔር አልመረጠውም አለ። |
የእሴይም ሦስቱ ታላላቆች ልጆቹ ሳኦልን ተከትለው ወደ ሰልፉ ሄደው ነበር፤ ወደ ሰልፉም የሄዱት የሦስቱ ልጆች ስም ይህ ነበረ፤ ታላቁ ኤልያብ፥ ሁለተኛውም አሚናዳብ፥ ሦስተኛውም ሣማዕ ነበረ።
የቂርያትይዓሪም ሰዎችም መጥተው የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት አወጡ፤ በኮረብታውም ላይ ወዳለው ወደ አሚናዳብ ቤት አገቡአት፤ የእግዚአብሔርንም ታቦት እንዲጠብቅ ልጁን አልዓዛርን ቀደሱት።