እግዚአብሔርም የሕፃኑን ጩኸት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የልጅሽን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ።
1 ሳሙኤል 11:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ ሳኦል ከእርሻው አርፍዶ መጣ፤ ሳኦልም፥ “ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ፣ ሳኦል በሬዎቹን እየነዳ ከዕርሻ ተመለሰ፤ እርሱም፣ “ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ሳኦል በሬዎቹን እየነዳ ከእርሻ ተመለሰ፤ እርሱም፥ “ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም የያቢሽ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል በዚህ ጊዜ ጥንድ በሬዎቹን ይዞ ከዋለበት እርሻ በመመለስ ላይ ነበር፤ እርሱም “ምንድን ነው ነገሩ? ሰው ሁሉ የሚያለቅሰው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ፤ እነርሱም ከያቤሽ የመጡ መልእክተኞች የሚሉትን ወሬ ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ሳኦል በሬዎቹን ተከትሎ ከእርሻው መጣ፥ ሳኦልም፦ ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው? አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት። |
እግዚአብሔርም የሕፃኑን ጩኸት ሰማ፤ የእግዚአብሔርም መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ ሲል ጠራት፥ “አጋር ሆይ፥ ምን ሆንሽ? እግዚአብሔር የልጅሽን ድምፅ ባለበት ስፍራ ሰምቶአልና አትፍሪ።
ከዚያም ሄደ፤ የሣፋጥንም ልጅ ኤልሳዕን በዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬዎች ሲያርስ፥ እርሱም ከዐሥራ ሁለተኛው ጋር ሆኖ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ አልፎ መጐናጸፊያውን ጣለበት።
ከብንያም ልጆች ስሙ ቂስ የተባለ አንድ ሰው ነበረ፥ እርሱም የአብሔል ልጅ፥ የያሬድ ልጅ፥ የባሔር ልጅ፥ የብንያም ሰው፥ የአፌቅ ልጅ፥ ጽኑዕ ኀያል ሰው ነበረ።