ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶርም ተመለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞች እሄዳለሁ” አለው። ዮቶርም ሙሴን፥ “በደኅና ሂድ” አለው።
1 ሳሙኤል 10:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም ለቤተ ሰቡ፥ “አህዮች እንደ ተገኙ ገለጠልን” አለው፤ ነገር ግን የመንግሥትን ነገር አላወራለትም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳኦልም መልሶ፣ “አህዮቹ መገኘታቸውን ገልጾ ነገረን” አለው። ይሁን እንጂ ስለ መንገሡ ሳሙኤል የነገረውን ለአጎቱ አልተናገረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳኦልም መልሶ፥ “አህዮቹ መገኘታቸውን ገልጦ ነገረን” አለው። ነገር ግን ስለ መንገሡ ሳሙኤል የነገረውን ለአጎቱ አልተናገረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦልም “የአህዮቹን መገኘት ነግሮናል” ሲል መለሰለት፤ ነገር ግን ንጉሥ ስለ መሆኑ ሳሙኤል የነገረውን ሁሉ ለአጐቱ አላወራለትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳኦልም አጎቱን፦ አህዮች እንደ ተገኙ ገለጠልን አለው፥ ነገር ግን ሳሙኤልን የነገረውን የመንግሥትን ነገር አላወራለትም። |
ሙሴም ሄደ፤ ወደ አማቱ ወደ ዮቶርም ተመለሰ፥ “እስከ ዛሬ በሕይወት እንደ አሉ አይ ዘንድ ተመልሼ ወደ ግብፅ ወደ ወንድሞች እሄዳለሁ” አለው። ዮቶርም ሙሴን፥ “በደኅና ሂድ” አለው።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በእርሱ ላይ አደረ፤ የፍየል ጠቦትን እንደሚጥልም ጣለው፤ በእጁም እንደ ኢምንት ሆነ፤ ያደረገውንም ለአባቱና ለእናቱ አልተናገረም።
ወስዶም በላ፤ እየበላም ሄደ፤ ወደ አባቱና ወደ እናቱም ደረሰ፤ ሰጣቸውም፤ እነርሱም በሉ፤ ማሩንም ከአንበሳው አፍ ውስጥ እንዳወጣው አልነገራቸውም።
ከሦስት ቀንም በፊት የጠፉ አህዮችህ ተገኝተዋልና ልብህን አታስጨንቀው። የእስራኤል መልካም ምኞት ለማን ነው? ለአንተና ለአባትህ ቤት አይደለምን?” አለው።
እነርሱም በከተማዪቱ ዳር ሲወርዱ ሳሙኤል ሳኦልን፥ “ብላቴናው ወደ ፊታችን እንዲያልፍ እዘዘው፤ አንተ ግን ከእኔ ጋር ከዚህ ቁምና የእግዚአብሔርን ቃል ስማ” አለው። ብላቴናውም አለፈ።