La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ሳሙኤል 1:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ባልዋ ሕል​ቃ​ናም፥ “ሐና ሆይ!” አላት እር​ስ​ዋም፥ “ጌታዬ እነ​ሆኝ” አለ​ችው። እር​ሱም፥ “ለምን ታለ​ቅ​ሻ​ለሽ? ለም​ንስ አት​በ​ዪም? ለም​ንስ ልብሽ ያዝ​ን​ብ​ሻል? እኔስ ከዐ​ሥር ልጆች አል​ሻ​ል​ሽ​ምን?” አላት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ባሏ ሕልቃናም እርሷን፣ “ሐና ሆይ፤ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ባሏ ሕልቃናም እርሷን፥ “ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትበዪም? ልብሽስ ለምን ያዝናል? ከዐሥር ወንዶች ልጆች እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህም የተነሣ ባልዋ ሕልቃና “ሐና ሆይ! ስለምን ታለቅሻለሽ? ስለምንስ አትመገቢም? ስለምንስ ዘወትር ይህን ያኽል ታዝኚአለሽ? ከዐሥር ልጆች ይልቅ እኔ አልበልጥብሽምን?” ይላት ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ባልዋም ሕልቃና፦ ሐና ሆይ፥ ለምን ታለቅሻለሽ? ለምንስ አትቀምሺም? ለምንስ ልብሽ ያዝንብሻል? እኔስ ከአሥር ልጆች አልሻልልሽምን? አላት።

Ver Capítulo



1 ሳሙኤል 1:8
11 Referencias Cruzadas  

አዛ​ሄ​ልም፥ “ጌታ​ዬን ምን ያስ​ለ​ቅ​ሰ​ዋል?” አለ። ኤል​ሳ​ዕም፥ “በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ላይ የም​ታ​ደ​ር​ገ​ውን ክፋት ስለ​ማ​ውቅ ነው፤ ምሽ​ጎ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ሳት ታቃ​ጥ​ላ​ለህ፤ ጐል​ማ​ሶ​ቻ​ቸ​ው​ንም በሰ​ይፍ ትገ​ድ​ላ​ለህ፤ ሕፃ​ና​ቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትፈ​ጠ​ፍ​ጣ​ለህ፤ እር​ጉ​ዞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ትሰ​ነ​ጥ​ቃ​ለህ፤” አለው።


ምሕ​ረቱ ቸል አለኝ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ጐ​በ​ኘ​ኝም አል​ተ​መ​ለ​ከ​ተ​ኝም።


አም​ላ​ኬና ንጉሤ አንተ ነህ፤ ለያ​ዕ​ቆብ መድ​ኀ​ኒ​ትን ያዘ​ዝህ።


አንቺ ያል​ወ​ለ​ድሽ መካን ሆይ፥ ደስ ይበ​ልሽ፤ አንቺ ያላ​ማ​ጥሽ ሆይ፥ እልል በዪ፤ ጩኺም፤ ባል ካላት ይልቅ ፈት የሆ​ነ​ቺቱ ልጆች በዝ​ተ​ዋ​ልና፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተተ​ወ​ችና እንደ ተበ​ሳ​ጨች፥ በል​ጅ​ነ​ቷም እንደ ተጠ​ላች ሴት የጠ​ራሽ አይ​ደ​ለም፥ ይላል አም​ላ​ክሽ።


እነ​ዚያ መላ​እ​ክ​ትም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል?” አሉ​አት፤ እር​ስ​ዋም፥ “ጌታ​ዬን ከመ​ቃ​ብር ውስጥ ወስ​ደ​ው​ታል፤ ወዴ​ትም እንደ ወሰ​ዱት አላ​ው​ቅም” አለ​ቻ​ቸው።


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም፥ “አንቺ ሴት፥ ምን ያስ​ለ​ቅ​ስ​ሻል? ማን​ንስ ትሺ​ያ​ለሽ?” አላት፤ እር​ስዋ ግን የአ​ት​ክ​ልት ቦታ ጠባቂ መስ​ሎ​አት፥ “ጌታዬ፥ አንተ ወስ​ደ​ኸው እንደ ሆነ ሄጄ ወደ እኔ እን​ዳ​መ​ጣ​ውና ሽቱ እን​ድ​ቀ​ባው ወዴት እንደ አኖ​ር​ኸው ንገ​ረኝ” አለ​ችው።


ወንድሞች ሆይ! እንመክራችኋለን፤ ያለ ሥርዐት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።


ከሰባትም ወንዶች ልጆች ይልቅ ለአንቺ ከምትሻል ከምትወድድሽ ምራት ተወልዶአልና ሰውነትሽን ያሳድሰዋል፥ በእርጅናሽም ይመግብሻል አሉአት።


በየ​ዓ​መ​ቱም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሚ​ወ​ጣ​በት ጊዜ እን​ዲህ ያደ​ርግ ነበር፤ እር​ስ​ዋም ትበ​ሳ​ጭና ታለ​ቅስ ነበር። እህ​ልም አት​በ​ላም ነበር።