ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጤያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘለዓለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።
1 ነገሥት 13:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ያን ሰምቶ፥ “በእግዚአብሔር ቃል ላይ ያመፀ ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ይህን ሲሰማ፣ “ይህ የእግዚአብሔርን ቃል ያቃለለው ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ቃል መሠረት አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገድሎታል” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ “ይህ የጌታን ቃል ያቀለለው ያ ጌታ ሰው ነው፤ ጌታ ባስጠነቀቀው መሠረት አሳልፎ ሰጥቶት አንበሳ ሰብሮ ገድሎታል” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሽማግሌው ነቢይ ይህን በሰማ ጊዜ “ያ ሰው የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ያልጠበቀው ነቢይ መሆን አለበት! ስለዚህም እግዚአብሔር ለአንበሳ አሳልፎ ሰጥቶታል ማለት ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያም ከመንገድ የመለሰው ነቢይ ያን በሰማ ጊዜ “በእግዚአብሔር አፍ ላይ ያመፀ ያ የእግዚአብሔር ሰው ነው፤ እግዚአብሔር እንደ ተናገረው ቃል፥ እግዚአብሔር ለአንበሳ አሳልፎ ሰጥቶታል፤ ሰብሮም ገድሎታል፤” አለ። |
ስለዚህም አቃልለኸኛልና፥ የኬጤያዊውንም የኦርዮን ሚስት ለአንተ ሚስት ትሆን ዘንድ ወስደሃልና ለዘለዓለም ከቤትህ ሰይፍ አይርቅም።
ነገር ግን በዚህ ነገር ለእግዚአብሔር ጠላቶች መነሣሣት ምክንያት አድርገሃልና ስለዚህ ደግሞ የተወለደልህ ልጅ ፈጽሞ ይሞታል” አለው።
እነሆም፥ መንገድ አላፊ ሰዎች ሬሳውን በመንገዱ ወድቆ፥ አንበሳውም በሬሳው አጠገብ ቆሞ አዩ፤ ገብተውም ሽማግሌው ነቢይ ይኖርበት በነበረው ከተማ አወሩ።
ሽማግሌውንና ጎበዙን፥ ድንግሊቱንም፥ ሕፃናቱንና ሴቶቹን፥ ፈጽማችሁ ግደሉ፤ ነገር ግን ምልክቱ ወደ አለበት ሰው ሁሉ አትቅረቡ፤ በመቅደሴም ጀምሩ” አላቸው። በቤቱም አንጻር ባሉ ሽማግሌዎች ጀመሩ።
ሙሴም አሮንን፥ “እግዚአብሔር፦ ወደ እኔ በሚቀርቡ እመሰገናለሁ፤ በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ ብሎ የተናገረው ይህ ነው” አለው፤ አሮንም ደነገጠ።
ፍርድ ከእግዚአብሔር ቤት ተነሥቶ የሚጀመርበት ጊዜ ደርሶአልና፤ አስቀድሞም በእኛ የሚጀመር ከሆነ ለእግዚአብሔር ወንጌል የማይታዘዙ መጨረሻቸው ምን ይሆን?