La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አዶ​ን​ያ​ስም በጎ​ች​ንና በሬ​ዎ​ችን፥ ጠቦ​ቶ​ች​ንም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ባለ​ችው በዞ​ሔ​ሌት ድን​ጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ወን​ድ​ሞ​ቹን ሁሉ፥ የን​ጉ​ሡ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ኀያ​ላን ሁሉ ጠራ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም አዶንያስ በዓይንሮጌል አቅራቢያ ባለው የዞሔልት ድንጋይ አጠገብ በጎችን፣ በሬዎችንና የሠቡ ጥጆችን ሠዋ፤ ወንድሞቹን ሁሉ፣ የንጉሡን ልጆች እንዲሁም የቤተ መንግሥቱ ሹማምት የነበሩትን የይሁዳ ሰዎች ሁሉ ጠራ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን ፍሪዳዎችንም በዔንሮጌል አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይጋ ሠዋ፥ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም ባርያዎች፥ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንድ ቀን አዶንያስ “ዔንሮጌል” ተብሎ በሚጠራው የውሃ ምንጭ አጠገብ የዞሔሌት አለት በሚባለው ስፍራ በጎችን፥ በሬዎችንና የሰቡ ወይፈኖችን ዐርዶ መሥዋዕት አቀረበ፤ የንጉሥ ዳዊትን ልጆችና በይሁዳ የሚገኙትን የመንግሥት ባለሥልጣኖች ሁሉ ወደዚህ ወደ መሥዋዕቱ በዓል መጥተው ተካፋዮች እንዲሆኑ ጋበዛቸው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አዶንያስም በጎችንና በሬዎችን ፍሪዳዎችንም በዓይንሮጌል አጠገብ ባለችው በዞሔሌት ድንጋይ ዘንድ ሠዋ፤ የንጉሡንም ልጆች ወንድሞቹን ሁሉ፥ የንጉሡንም ባሪያዎች፥ የይሁዳን ሰዎች ሁሉ ጠራ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 1:9
9 Referencias Cruzadas  

ዮና​ታ​ንና አኪ​ማ​ሆ​ስም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ቆመው ሳለ አን​ዲት ብላ​ቴና ሄዳ ነገ​ረ​ቻ​ቸው፤ ወደ ከተማ መግ​ባት አል​ተ​ቻ​ላ​ቸ​ውም ነበ​ርና፤ እነ​ር​ሱም ሄደው ለን​ጉሡ ለዳ​ዊት ነገ​ሩት።


እር​ሱም ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱ​ንም አለቃ ኢዮ​አ​ብን ጠር​ቶ​አል፤ ባሪ​ያ​ህን ሰሎ​ሞ​ንን ግን አል​ጠ​ራ​ውም።


እርሱ ዛሬ ወርዶ ብዙ በሬ​ዎ​ች​ንና ጠቦ​ቶ​ችን፥ በጎ​ች​ንም ሠው​ቶ​አል፤ የን​ጉ​ሡ​ንም ልጆች ሁሉ፥ የሠ​ራ​ዊ​ቱን አለቃ ኢዮ​አ​ብን፥ ካህ​ኑ​ንም አብ​ያ​ታ​ርን ጠር​ቶ​አል፤ እነ​ሆም፥ በፊቱ እየ​በ​ሉና እየ​ጠጡ፦ አዶ​ን​ያስ ሺህ ዓመት ይን​ገሥ ይላሉ።


የክፉዎች መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ የረከሰ ነው፤ የቅኖች ጸሎት ግን በእርሱ ዘንድ የተወደደ ነው።


ደግሞ ሌሎችን ባሮች ልኮ ‘የታደሙትን እነሆ፥ ድግሴን አዘጋጀሁ፤ ኮርማዎቼና የሰቡት ከብቶቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ተዘጋጅቶአል፤ ወደ ሰርጉ ኑ፤ በሉአቸው፤’ አለ።


ድን​በ​ሩም በአ​ኮር ሸለቆ አራ​ተኛ ክፍል ላይ ይወ​ጣል፤ በአ​ዱ​ሚን ዐቀ​በት ፊት ለፊት፥ በደ​ቡብ በኩል ወዳ​ለ​ችው ወደ ጌል​ገላ ይወ​ር​ዳል፤ ድን​በ​ሩም ወደ ፀሐይ ምንጭ ውኃ ያል​ፋል፤ መው​ጫ​ውም በሮ​ጌል ምንጭ አጠ​ገብ ነበረ፤


ድን​በ​ሩም በሄ​ኖም ሸለቆ ፊት ለፊት ወዳ​ለው ተራራ መጨ​ረሻ ወረደ፤ እር​ሱም በራ​ፋ​ይም ሸለቆ በሰ​ሜን በኩል ነው፤ ወደ ሄኖም ሸለቆ ወደ ኢያ​ቡስ ዳር በደ​ቡብ በኩል ወረደ፥ ወደ ሮጌል ምን​ጭም ወረደ።