እንዲህም ሆነ፤ አብራም ወደ ግብፅ ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤
1 ነገሥት 1:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቆንጆዪቱም እጅግ ውብ ነበረች፤ ንጉሡንም ታቅፈውና ታገለግለው ነበር፤ ንጉሡ ግን አያውቃትም ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልጃገረዲቱ እጅግ ቈንጆ ነበረች፤ ንጉሡንም ትንከባከበውና ታገለግለው ነበር፤ ንጉሡ ግን ከርሷ ጋራ ግንኙነት አልነበረውም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልጃገረዲቱም እጅግ ውብ ነበረች። ለንጉሡም ረዳትና አገልጋይ ሆነች፤ ንጉሡ ግን ከእርሷ ጋር ግንኙነት ፈጽሞ አያውቅም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም እጅግ ውብ ነበረች፤ ከንጉሡም ጋር ሆና በማገልገል ትንከባከበው ነበር፤ ይሁን እንጂ እርሱ ከእርስዋ ጋር አልተገናኘም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቆንጆይቱም እጅግ ውብ ነበረች፤ ንጉሡንም ትረዳውና ታገለግለው ነበር፤ ንጉሡ ግን አያውቃትም ነበር። |
እንዲህም ሆነ፤ አብራም ወደ ግብፅ ለመግባት በቀረበ ጊዜ ሚስቱን ሦራን እንዲህ አላት፥ “አንቺ መልከ መልካም ሴት እንደ ሆንሽ እነሆ እኔ አውቃለሁ፤
የአጊትም ልጅ አዶንያስ፥ “ንጉሥ እሆናለሁ” ብሎ ተነሣ፤ ሰረገሎችንና ፈረሰኞችን በፊቱም የሚሮጡ አምሳ ሰዎችን አዘጋጀ።
እርሱም፥ “ፊቱን አይመልስብሽምና፥ ሱነማዪቱን አቢሳን ይድርልኝ ዘንድ ለንጉሡ ለሰሎሞን እንድትነግሪው እለምንሻለሁ” አለ።